ዜጎች የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን በተገለጠ ልቦና ሊመለከቱ ይገባል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንጦጦ-ቀበና የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን በዛሬው ዕለት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምረቃው ወቅት እንደተናገሩት፤ የወደፊቱን ውበት አስቀድሞ በአእምሮ መሳል መቻል ለስራ ስኬታማነት ቁልፍ መንገድ መሆኑን አንስተዋል።
"መደመር" ማለት የዕውቀት፣ የፋይናንስ፣ የጉልበትና የአመራር ብቃትን በአንድነት ማዋሃድ መሆኑን ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዜጎች ተባብረውና ተደጋግፈው ከተነሱ ከቀበና የላቁ አስደናቂ ተአምራትን መሥራት እንደሚችሉ በተግባር መመስከሩን ገልጸዋል።
ይህ ግዙፍ ልማት የአዲስ አበባን ስልጣኔ ከፍ የሚያደርግና ከተማዋን ለአየር ንብረት መዛባት የማይበገሩ እንዲሁም ለነዋሪዎቿ እጅግ ምቹ ከሚያደርጉ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች አንዱ ነው ብለዋል።
አክለውም "ለዋና ከተማዋ ነዋሪዎች ዝቅጠት፣ መቆሸሽና በሌሎች አገራት ስልጣኔ መቅናት አይገባቸውም" ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ የአረንጓዴ ልማት ሲጀመር በርካቶች አይሳካላችሁም የሚል ድምፅ አሰምተው ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያውያን ግን ጥንታዊ የማንነት ጥባቸውንና ጽናታቸውን ተጠቅመው በተግባር በማሳየት ለተቺዎች የማይናወጥ ምላሽ መስጠታቸውን አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ ያላትን እምቅ ተፈጥሯዊ ለግስና በተደራጀ ዕይታ ማውጣት ባለመቻላችን ለዘመናት ማራኪ ገጽታዋ ተደብቆ መቆየቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ማኅበረሰቡ እነዚህን አገራዊ ስኬቶች በተገለጠ ልቦና እንዲመለከትና ለቀጣይ የጋራ ድሎች እንዲዘጋጅም ጥሪ አስተላልፈዋል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #pmabiy #addisababa #entotokebena #riverside #urbantransformation

4 months ago