1 month ago
ስለፍቅር በፍቅር እናመሰግናለን!” — ሐዋሳ ከተማ
* ለሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ የሀብት ማሰባሰብ ተከናወነ
“የዘራነው የትብብር ዘር ነገ የእድገት ዛፍ ይሆናል”
— ከንቲባ ጥራቱ በየነ
#ethiopia | የምሥራቅ አፍሪካ የስምጥ ሸለቆ ዕንቁና በተፈጥሮ የታደለችው የሐዋሳ ከተማ፣ የተፈጥሮ መስህቧን ከዘመናዊ ሰው ሠራሽ ጥበብ ጋር በማቀናጀት አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ውስጥ ትገኛለች።
በ1952 ዓ.ም የተቆረቆረችውና በሲዳምኛ ቋንቋ "ሰፊ መሬት" ከሚለው ታሪካዊ ስሟን ያገኘችው ይህች የቱሪዝምና የኢንዱስትሪ ማዕከል፣ በአሁኑ ወቅት በ157 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ ከ557,854 በላይ ነዋሪዎችን አቅፋ በኮሪደር ልማት ይበልጥ እየተዋበች ትገኛለች።
ይህንኑ ልማት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትናንት በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የመጀመሪያ ምዕራፍ የማጠቃለያ መድረክ፣ ለሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ የሀብት ማሰባሰብ በታላቅ ስኬት ተከናውኗል።
የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባስተላለፉት መልዕክት፣ "ሀዋሳ በሁላችን ዘንድ ተወዳጅና ተናፋቂ ከተማ ናት፤ ይህ ውበቷም አሁን ይበልጥ ደምቋል" ብለዋል። የሲዳማ ሕዝብ የፍቅርና የአብሮነት እሴት ከከተማዋ ወዳጆች ድጋፍ ጋር ተደምሮ እየተገነባ ያለው የሐይቅ ዳርቻ ልማት የከተማዋን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የቱሪዝም መዳረሻነቷን በእጅጉ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።
አያይዘውም መንግሥት የከተሞችን ዕድገት ለማፋጠን የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት የሕዝብና የባለሀብቶችን አቅም ማስተባበር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ በሐዋሳ የታየው የተቀናጀ የልማት እንቅስቃሴ በሌሎች ከተሞችም ሊተገበር የሚገባ አዎንታዊ ተሞክሮ መሆኑን ጠቁመዋል።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በበኩላቸው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተመዘገበው ይህ ስኬት ሐዋሳ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ያላትን ዝግጁነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል። "ሀዋሳ የደቡብ ፈርጥ፣ የሰላም ደሴት፣ በተፈጥሮዋ ምድረ ገነት እንዲሁም በሕዝቧ እንግዳ ተቀባይነት የፍቅር ቤት ናት" ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ፍጥነትና ቁርጠኝነት እየተከናወነ ያለው 4ኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ሥራ ከተማዋን የሥልጣኔና የውበት ማማ ለማድረግ ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝና ባለሀብቶች ይህንን ዕድል እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርበዋል።
* የሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ምን ይዟል?
የከተማዋን የተፈጥሮ ጸጋ ከዘመናዊ መሠረተ ልማት ጋር በማቀናጀት ወደ ላቀ የሥልጣኔ ማማ የሚያሸጋግረውና ከጥቁር ውኃ እስከ ታቦር ተራራ ድረስ 12 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነው ይህ ፕሮጀክት ከተጀመረ ሦስት ወራት ተቆጥረዋል።
በ6 ወራት ውስጥ በጥራት ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የታቀደው ፕሮጀክት የሚከተሉትን ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች አካቷል፦
* ሰፊ የእግር መንገድ አማራጮች
* ቀድሞ ከነበሩት ጠባብ መንገዶች በተለየ ሰፊና ዘመናዊ የእግር መንገድ መሄጃዎች።
* የብስክሌት መንገዶች
* ለትራንስፖርትና ለስፖርት ምቹ የሆኑ ልዩ የብስክሌት መስመሮች።
* ዘመናዊ የደህንነት ካሜራዎች (CCTV)
* የከተማዋንና የመንገዶቹን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የተዘረጋ የቁጥጥር ሥርዓት።
* አረንጓዴ የፓርክ ስፍራዎች
* በመንገዶቹ ዳርቻ የተተከሉ ዛፎች፣ አበቦችና የተሰሩ የፓርክ ቦታዎች።
ልማቱ የሐዋሳ ሐይቅን የተፈጥሮ ሥነ-ምህዳር፣ የውኃ ውስጥ እንስሳትን፣ ጉማሬዎችን እንዲሁም ከ30 ዓመታት በላይ ከነዋሪው ጋር በሰላም የኖሩትን እንደ ጃንቦ፣ ሻርክ፣ ኮኮብ እና ዝንጀሮ ወፍ ያሉ የከበሩ የአእዋፋት ዝርያዎችን በጠበቀና በተንከባከበ መልኩ የሚከናወን በመሆኑ ለከተማዋ ልዩ ተፈጥሯዊ መስህብን ያጎናጽፋታል።
“የዘራነው የትብብር ዘር ነገ የእድገት ዛፍ ይሆናል”
— ከንቲባ ጥራቱ በየነ
የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ለፕሮጀክቱ መሳካት የላቀ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ሁሉ የከበረ ምስጋና አቅርበው፣ “ዛሬ ለሐዋሳ ሐይቅ ልማት ያደረጋችሁት አስተዋጽኦ የሐዋሳን የወደፊት ዕድገት የሚያፋጥን ታሪካዊ እርምጃ ነው። ያበረከታችሁት መዋጮ ወደ ውብ የሐይቅ ዳርቻ፣ ወደ አረንጓዴ ሕዝባዊ ስፍራዎች፣ ወደ ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችና ወደ ሥራ ፈጠራ ይቀየራል” ብለዋል።
እንደ ከንቲባው ገለጻ፣ ለፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ 3.2 ቢሊዮን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 1.5 ቢሊዮን ብሩ በሕዝብ፣ በባለሀብቶችና በሐዋሳ ወዳጆች አጋርነት ለመሰብሰብ ታቅዶ አሁን ላይ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ የፍቅር ሐይቅ፣ የአሞራ ገደልና የአሳ ገበያ አካባቢዎች የሚለሙ ሲሆን፣ ዘመናዊ የእግረኛ መንገዶች፣ የብስክሌት መስመሮች፣ የመዝናኛ ስፍራዎችና የጀልባ ማረፊያዎች ይገነባሉ።
የከተማ አስተዳደሩ የተጣለበትን አደራ በግልጽነት፣ በተጠያቂነትና በከፍተኛ ታማኝነት በመወጣት ፕሮጀክቱን በተቀመጠለት ጊዜና ጥራት ለማጠናቀቅ በትጋት እንደሚሠራ ያረጋገጡት ከንቲባው፤ ፕሮጀክቱ ሐዋሳን የአፍሪካ ተመራጭ የቱሪዝምና የኮንፍረንስ ከተማ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተምሳሌት (MODEL) የማድረግ ራዕይን እውን ለማድረግ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።
ባለሀብቶች ወደ ሀዋሳ በመምጣት እውቀትና ሀብታቸውን ተጠቅመው በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘኩራ ሚዲያና ፕሮሞሽን ለአገርና ለሕዝብ እንዲሁም ለሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት የሀብት ማሰባሰቢያ ያደረገውን አስተዋጽኦ ታላቅ ምስጋና ተችሮታል።
በሀገራዊ የገቢ ማሰባሰቢያ እና የምስጋና ፕሮግራም ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ተመስገን ጥሩነህ የተናገሩት፦
“ታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ከመንግሥት ድጋፍ ባለፈ የሁሉንም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ እገዛና ትብብር ይሻሉ”
ለዚህ ትልቅ ራዕይ መሳካት እያንዳንዱ ዜጋ በገንዘቡ፣ በእውቀቱና በጉልበቱ የሚያበርክተው አስተዋፅዖ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የተጀመረው የሐይቅ ዳርቻ ልማት የውበት ሥራ ብቻ ሳይሆን ሰፊ የቱሪዝም፣ የኢኮኖሚ፣ የሥራ ፈጠራና የአካባቢ ጥበቃን ያቀፈ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስገንዝበዋል።
ታላላቅ ፕሮጀክቶች በመንግሥት ጥረት ብቻ ሊሳኩ ስለማይችሉ የሕዝባችን፣ የግሉ ዘርፍ፣ የምሁራንና የዳያስፖራው ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት የሚደረገው ድጋፍ ከገንዘብ ባሻገር እውቀትን፣ ልምድንና በጎ ተጽዕኖን ማካተት ይኖርበታል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የከተማዋን የመዝናኛ፣ የንግድና የመኖሪያ ሥፍራነት ወደ ላቀ ምዕራፍ በማሸጋገር ሀዋሳን በምስራቅ አፍሪካ ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ እንደሚያደርጋትም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
#ሐዋሳ #የኮሪደርልማት #የሐይቅዳርቻልማት #ቱሪዝም #ኢትዮጵያ #hawassa_sidaama #lakehawassa #riverside #corridordesign

u12e8u1240u1260u1293 u12c8u1295u12dd u12f3u122du127b u120du121bu1275 u121du1295 u121du1295 u12a0u12abu1277u120d?
#ethiopia #kebenariver #cleanriver #riverside #development ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
የቀበና ወንዝ ዳርቻ ልማት ምን ምን አካቷል?
#ethiopia #kebenariver #cleanriver #riverside #development
1 month ago
ዜጎች የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን በተገለጠ ልቦና ሊመለከቱ ይገባል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንጦጦ-ቀበና የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን በዛሬው ዕለት መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምረቃው ወቅት እንደተናገሩት፤ የወደፊቱን ውበት አስቀድሞ በአእምሮ መሳል መቻል ለስራ ስኬታማነት ቁልፍ መንገድ መሆኑን አንስተዋል።
"መደመር" ማለት የዕውቀት፣ የፋይናንስ፣ የጉልበትና የአመራር ብቃትን በአንድነት ማዋሃድ መሆኑን ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዜጎች ተባብረውና ተደጋግፈው ከተነሱ ከቀበና የላቁ አስደናቂ ተአምራትን መሥራት እንደሚችሉ በተግባር መመስከሩን ገልጸዋል።
ይህ ግዙፍ ልማት የአዲስ አበባን ስልጣኔ ከፍ የሚያደርግና ከተማዋን ለአየር ንብረት መዛባት የማይበገሩ እንዲሁም ለነዋሪዎቿ እጅግ ምቹ ከሚያደርጉ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች አንዱ ነው ብለዋል።
አክለውም "ለዋና ከተማዋ ነዋሪዎች ዝቅጠት፣ መቆሸሽና በሌሎች አገራት ስልጣኔ መቅናት አይገባቸውም" ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ የአረንጓዴ ልማት ሲጀመር በርካቶች አይሳካላችሁም የሚል ድምፅ አሰምተው ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያውያን ግን ጥንታዊ የማንነት ጥባቸውንና ጽናታቸውን ተጠቅመው በተግባር በማሳየት ለተቺዎች የማይናወጥ ምላሽ መስጠታቸውን አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ ያላትን እምቅ ተፈጥሯዊ ለግስና በተደራጀ ዕይታ ማውጣት ባለመቻላችን ለዘመናት ማራኪ ገጽታዋ ተደብቆ መቆየቱን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ማኅበረሰቡ እነዚህን አገራዊ ስኬቶች በተገለጠ ልቦና እንዲመለከትና ለቀጣይ የጋራ ድሎች እንዲዘጋጅም ጥሪ አስተላልፈዋል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #pmabiy #addisababa #entotokebena #riverside #urbantransformation

እንጦጦ እስከ ቀበና የወንዝ ዳርቻ ሲገለጥ
Entoto to Kebena Riverside Unveiled
የእንጦጦ–ቀበና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ተመረቀ
#ethiopia | የአዲስ አበባን ስነ-ምህዳር፣ ቱሪዝምና ኢኮኖሚ ለማጠናከር የታለመ ግዙፍ ፕሮጀክት
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ የተመረቀው የእንጦጦ–ቀበና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት፣ የአዲስ አበባን የከተማ ገጽታ ከማሻሻል ባለፈ የስነ-ምህዳር ጥበቃ፣ የመሰረተ ልማት ማሻሻያ እና የኢኮኖሚ ዕድሎችን ለማስፋፋት የታለመ ትልቅ ፕሮጀክት ነው።
ፕሮጀክቱ የወንዝ ተፋሰስን በማልማትና ከተማዋን ለነዋሪዎች እና ለጎብኚዎች የተሻለች ለማድረግ የሚያግዙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን አካትቷል።
የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ክፍሎች
የወንዝ ልማት
- 1 ትልቅ ግድብ
- 16 አነስተኛ ግድቦች
- 3 ቼክ ዳሞች
- 20.2 ኪሎ ሜትር የድጋፍ ግንብ
የወንዝ ዳርቻ ጥበቃ
- 36.9 ኪሎ ሜትር የአፈርና የስነ-ምህዳር ጥበቃ ሥራዎች፣ የኮንሶ ጋቢዮን እና እርከን ሥራዎችን ጨምሮ።
አረንጓዴ ልማት
- 59.7 ሄክታር አረንጓዴ ሽፋን
- 50,330 ዛፎች ተተክለዋል
የተቀናጀ መሰረተ ልማት
- 21 የእግረኛ ድልድዮች
- 33.2 ኪሎ ሜትር የውስጥ መንገዶች
- የፍሳሽ መስመር
- 695 ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግዱ 7 የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች ናቸው።

Sponsored by
Surafel
2 months ago
2 months ago
u12dbu122c u12e8u1270u1218u1228u1240u12cd u12a8u12a5u1295u1326u1326 u12a5u1235u12a8 u1240u1328u1294 u1218u12f5u1283u1294u12d3u1208u121d u12ebu1208u12cd u12e8u1218u120du1236 u121bu120du121bu1275 u12e8u12c8u1295u12dd u12f3u122du127b u120du121bu1275 u12a0u1235u1218u120du12adu1276 u12a8u1295u1272u1263u12cb u12e8u1270u1293u1308u1229u1275 #addisababa #riverside #development ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ዛሬ የተመረቀው ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለው የመልሶ ማልማት የወንዝ ዳርቻ ልማት አስመልክቶ ከንቲባዋ የተናገሩት #addisababa #riverside #development
2 months ago
2 months ago
u12edu1214 u1208u12a2u1275u12eeu1335u12eb u1275u120du1245 u1265u1235u122bu1275 u1290u12cd
#pmabiyahmed #riverside #coridordevelopment ","delight_ranges":[],"image_ranges":[],"inline_style_ranges":[],"aggregated_ranges":[],"ranges":[{"entity":{"__typename":"Hashtag","__isEntity":"Hashtag","url":"https://www.facebook.com/h...
ይሔ ለኢትዮጵያ ትልቅ ብስራት ነው
#pmabiyahmed #riverside #coridordevelopment
Comments