ፈረንሳይ ኖርዌይን አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጥምር አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው 23ኛው የዓለም ዋንጫ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ፈረንሳይ ኖርዌይን 4 ለ 1 አሸንፋለች።
በምድብ ዘጠኝ ያደረጓቸውን ሁለቱንም ጨዋታዎች በማሸነፍ አስቀድመው 32ቱን የተቀላቀሉት ፈረንሳይ እና ኖርዌይ ምሽት 4 ሰዓት ተገናኝተው፤ ፈረንሳይ በማሸነፏ 9 ነጥብ በመያዝ ምድቡን በበላይነት አጠናቅቃለች፡፡
የፈረንሳይን ሶስት ግቦች ኦስማን ዴምቤሌ በማስቆጠር ሃት-ሪክ የሰራ ሲሆን፤ አራተኛውን ግብ ዱዌ አስቆጥሯል።
የኖርዌይን ብቸኛ ግብ አስጋርድ ከመረብ አገናኝቷል።
በዚሁ ምድብ በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ኢራቅን የገጠመችው አፍሪካዊቷ ሀገር ሴኔጋል 5 ለ 0 በማሸነፍ ምርጥ ሦስተኛ በመሆን 32ቱን ለመቀላቀል የሚያስችላትን ዕድል ፈጥራለች።

1 month ago