Logo
EBC
የኢትዮጵያ የ5 ዓመት ስኬታማ ጉዞ፦ ከግብርና እስከ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ
*************

ባለፉት 5 ዓመታት በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የተጀመረው የብልፅግና ጉዞ የትውልድ ተስፋን ያለመለመ እና የነገዋን ኢትዮጵያ ምሥል በግልጽ የሚያሳዩ ስኬቶች የተመዘገቡበት ነው።

ይህ ጉዞ ከመሠረተ ልማት እስከ ማኅበራዊ አገልግሎቶች፣ ከኢኮኖሚ ግንባታ እስከ ግብርና ምርታማነት ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል።

የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ሥራዎች የዘርፉን አቅም ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግረዋል።

በተለይ የመኸር ስንዴ ልማት እና የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ፕሮግራሞች የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተወሰዱ ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው።

በቴክኖሎጂ የተደገፈ የግብርና አሠራር አርሶ አደሩን ከባህላዊ አሠራር በማላቀቅ ምርታማነትን በእጥፍ ማሳደግ አስችሏል።

ይህ የዘርፉ ስኬት ለኢንዱስትሪ ልማት የሚያስፈልገውን ግብዓት በማቅረብ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

ሁለንተናዊ ብልጽግናን እውን ለማድረግ የተከናወኑ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችም የውስጥ ሀብትን በአግባቡ በመጠቀም የላቀ ውጤት ለማምጣት አስችለዋል።

የምርት እና የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ በወጪ ንግድ ተወዳዳሪነትን መፍጠር እና የሥራ ዕድልን ማስፋት መቻሉ የዚህ ስኬት መገለጫዎች ናቸው።

በተመሳሳይ በተለይ በትራንስፖርት፣ በኢነርጂ እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፎች የተከናወኑ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ በጠንካራ መሠረት ላይ እንዲቆም አድርገውታል።

ይህ የብልፅግና ጉዞ በቁሳዊ ሀብት ብቻ የሚለካ ሳይሆን የሕዝብን ማኅበራዊ ሕይወት በማሻሻል ጭምር የሚገለፅ ነው።

ትምህርትን ለሁሉም በማዳረስ፣ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን በማስፋት እና የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የደኅንነት መረቦችን በመዘርጋት ረገድም ውጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል።

ባለፉት 5 ዓመታት የተመዘገቡት እነዚህ ተጨባጭ ስኬቶች ቀጣይነት ያለው ልማት፣ አስተማማኝ ሰላም እና የጋራ መግባባትን እንደሚፈጥሩ ይጠበቃል።

በሃና ምንዳሁን
#ethiopia #growth #development #transformation #ebc

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.