(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ የተካሄደውም ብሄራዊ ምርጫ በተመለከተ መግለጫ አወጣ፡፡ በህብረቱ ኮሚሽነር መሀሙድ አሊ የሱፍ ስም የወጣው ይህ መግለጫ ጁን 1 ቀን 2026 የተካሄደው የኢትዮጵያ 7ተኛው ዙር አጠቃላይ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ የኢትዮጵያን ህዝብና መንግስት በማመስገን ጀምሯል፡፡
ሲቀጥልም ‹‹የምርጫ ሂደቱ ኢትዮጵያዊያን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት መሰረት የሆነውን ዲሞክራሲ የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት አሳይቷል›› ያለው መግለጫው ኮሚሽነሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ብቃትና ቁርጠኝነት ማድነቃቸውንም አስረድቷል፡፡
አስከትሎም ይፋ በሆነው የምርጫው ውጤት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ብልፅግና ፓርቲ በአብላጫ ድምፅ በማሸነፋቸው ኮሚሽነሩ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ማስተላለፋቸውን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽነሩ በዚህ መልእክታቸው የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለማጠናከር ታማኝነት ያለው፣ ሰላማዊና ግልፅ የምርጫ ሂደቶችን እንዲከተሉ ማሳሰባቸውን መግለጫው አስረድቷል፡፡

1 month ago