Logo
Tigu S Alemayew
በጣም የሚያምር ፎቶ💙 እንደዚህ ሰው በህይወት እያለ ሲከበር እና ሲወደድ ደስ ይላል

ተዋናይ ዳንኤል አሸናፊ ( ዳኒ ፂሞ ) #በሰይፉ_ሾው

★ ከፊልምና ቴአትር ስራ በቃኝ ብዬ የተውኩት
ስለራበኝ ነው።

#ልጄስ ተከታታይ ድራማ በአለም አቀፍ ደረጃ
ታጭቶ ተሸልሟል።

★ ጀርባዬን ከ20 ዓመት በፊት ሰርጀሪ ተሰርቼው
የህክምና ስህተት ተፈፅሞብኛል።

★ ሰርጀሪውን አበላሽተው ስለሰሩኝ ቤት ከተቀመጥኩኝ
1 ዓመት ከ10 ወር ሆነኝ። አንድ ቴአትር ግን
ማስታገሻ እየወሰድኩኝ ነው የምሰራው።

★ ከህንድ የመጡ ሀኪሞች እኛ ጋር ና እንሰራሃለን
ብለውኛል።

★ ወታደር ቤት ገብቼ ሳይመቸኝ ወጣሁ። ከወታደር
ቤት ወጥቼ ወደትውልድ ሀገሬ ጅማ ድረስ
በእግሬ ተጉዣለሁ።

★ ቴአትር መስራት የጀመርኩት ጅማ ውስጥ
የምናገለግልበት ቤ/ክርስቲያን ነው።

★ ከዚህ በፊት ብየዳ ፣ ሸክም ( ወዛደርነት ) እና
የመንገድ አስፓልት ስራ ሰርቻለሁ።

★ በዚህ ሙያ ስትኖር ይከብድሃል።

★ የእኛ ስራ መድረክ ላይ ተጨብጭቦልህ በእግርህ
ወደ ቤትህ ትገባለህ።

★ ከጀርባ ህመሜ ጋር ተያይዞ በታክሲ መሄድ
አልችልም። በራይድ እየተመላለስኩኝ ነው
የምሰራው።

★ እንኳን ሰራሁት ብዬ የምኮራበት ስራ
ልጄስ ተከታታይ ድራማ ነው።

★ ከቴአትር እጅግ ወድጄው የሰራሁት ደግሞ
ሲራኖ ቴአትር ነው።

★ ከ10 በላይ ቴአትር ሰርቻለሁ። ፊልሞች
ደግሞ ወደ 20 ገደማ ሰርቻለሁ።

★ እኔ እስካሁን አልሰራሁም ወይ እንድል ያደረገኝ
ልጄስ ድራማ ነው።

አርቲስት ሚኪያስ መሐመድ ለዳኒ ፂሞ
100,000.00 ( መቶ ሺህ ብር ) ሰጥቶታል።
ሚኪ ባለታክሲው ይመችህ ✌

በተለያዩ የትወና ጥበቡ ያስደመመን
ተዋናይ ዳንኤል አሸናፊ ( ዳኒ ፂሞን ) ለመርዳት
የምትፈልጉ ፦

1000343965037
CBE
ዳንኤል አሸናፊ

Share ሼር በማድረግም ምርጡን ተዋናይ
ሰው እንዲያግዘው እናድርግ 🙏

Dani Tsimo
ተዋናይ ዳኒኤል አሸናፊ ፦ ለሰጠኸን ምርጥ ስራዎች
እናመሰግናን። ከህመምህ አገግመህ ወደሙሉ ጤንነትህ
እንድትመለስ ፈጣሪ ይርዳህ !

ዘሪሁን ተዝናኑ ከፃፈው ላይ የተወሰድ

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.