Logo
Getu Temesgen
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያልተጋበዙበት የኦባማ ድግስ
#ethiopia | ባራክ እና ሚሼል ኦባማ በሺካጎ ከተማ የተገነባውን እና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን “የኦባማ ፕሬዚዳንታዊ ማዕከል” በይፋ ለመመረቅ መድረክ ላይ ተገኝተዋል።

ማዕከሉ ነገ “ጁንቲንዝ” በተሰኘው አገራዊ የነፃነት በዓል ዕለት ለሕዝብ ክፍት እንደሚሆን ታውቋል።​በዛሬው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የቀድሞዎቹ ፕሬዚዳንቶች ቢል ክሊንተን፣ ጆርጅ ደብሊው ቡሽ እና ጆ ባይደን የተገኙ ሲሆን፣ የቀድሞዋ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስም በሥፍራው ታድመዋል።

ይሁን እንጂ ከፕሬዚዳንት ኦባማ ጋር የነበራቸው የቆየ አለመግባባት ወደ ዋይት ሃውስ ከመምጣታቸው በፊት የጀመረው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ግብዣ አልተደረገላቸውም።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

7 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.