Logo
EBC
ምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተ ምክክር ለዘላቂ የሀገር ግንባታ ወሳኝ ነው
************************

የአንድ ሀገር ህልውና ሊረጋገጥ የሚችለው በዜጎች መካከል በሚኖር የጋራ መግባባት እና ትብብር ላይ ነው።

ለዚህም በሀገራዊ ምክክር እና ሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ምክንያታዊነት ወሳኝና መሪ ሚና ይጫወታል።

በምክክር አውድ ውስጥ ምክንያታዊነት ሲባል ከስሜታዊነት፣ ከጥላቻ እና ከቂም በጸዳ መልኩ አመክንዮንና ማስረጃን መሰረት ማድረግ ማለት ነው።

ይህ መርህ ዜጎች በሀገራቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ዘላቂ መፍትሄዎችን በሰከነ መንፈስ እንዲፈልጉ ያስችላቸዋል።

ምክንያታዊነት ዜጎች ከጥላቻ ንግግሮች በመራቅ በምክክሩ ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ ሚዛናዊ ውይይቶች እንዲካሄዱ በር ይከፍታል።

በሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ላይ እና በመሰረታዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ ያሉ ልዩነቶችን ማጥበብ የሚቻለው በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ሰላማዊ ውይይት ብቻ ነው።

በጠረጴዛ ዙሪያ የሚደረግ ድርድር ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ ብቸኛው የችግሮች መፍቻ ቁልፍ ነው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሚያካሂደው ዋና የምክክር መድረክ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በባለቤትነት በማሳተፍ ዘላቂ ብሄራዊ መግባባት የመፍጠር እምቅ አቅም አለው።

ሀገራዊ ምክክሩ የጥቂት ልሂቃን ሳይሆን የሁላችንም የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወሰንበት ብሄራዊ መድረክ ነው።

በመሆኑም እያንዳንዱ ዜጋ ምክንያታዊነትን መሰረት አድርጎ ሂደቱን በቅንነት የመደገፍ እና ለስኬታማነቱ የበኩሉን አስተዋጽኦ የማበርከት ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።

በብሌን ደምበሎ
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopia #national #dialogue

14 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.