(ዘ-ሐበሻ ዜና) በናይጄሪያ የቀድሞ የአቪዬሽን ሚኒስትር ሀዲ ሲሪካ የሙስና ክስ የፍርድ ሂደት ላይ "ናይጄሪያ ኤር" የተሰኘውን አዲስ ብሔራዊ አየር መንገድ ለማስተዋወቅ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ለጥቂት ቀናት ጥቅም ላይ ውሎ እንደነበር አንድ ምስክር ለአቡጃ ፍርድ ቤት አስረዱ።
የናይጄሪያ የኢኮኖሚ እና የፋይናንስ ወንጀሎች ኮሚሽን መርማሪ እና የዓቃቤ ሕግ 12ኛ ምስክር የሆኑት ክሪስቶፈር ኦዶፊን ለፍርድ ቤቱ እንዳብራሩት.. አውሮፕላኑ ከሜይ 27 እስከ 29 ቀን 2023 ድረስ ብቻ በናይጄሪያ ቆይታ አድርጓል። በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ በላዩ ላይ "ናይጄሪያ ኤር" የሚል የብራንድ ጽሑፍ ተለጥፎበት ለሕዝብ ዕይታ ከቀረበ በኋላ፣ ወዲያውኑ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ ጽሑፉ እንዲነሳ ተደርጓል። ምስክሩ አክለውም ይህ አሠራር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በተደረገ የቻርተር (የኪራይ) ስምምነት የተፈጸመ መሆኑን እና የበረራ አባላቱም የኢትዮጵያ አየር መንገድን የደንብ ልብስ ለብሰው እንደነበር ገልጸዋል።
አቃቤ ሕግ ይህ ድርጊት የቀድሞው ሚኒስትር በስልጣን ዘመናቸው ከብሔራዊ አየር መንገዱ ምሥረታ ጋር በተያያዘ ከፈጸሙት ሰፊ የኮንትራት አሰጣጥ ማጭበርበር አንዱ አካል መሆኑን ክስ አቅርቧል። ይሁን እንጂ የቀድሞው ሚኒስትር ሀዲ ሲሪካ፣ አብረዋቸው የተከሰሱት ልጃቸው ፋጢማ ሲሪካ፣ አማቻቸው እና ሌሎች ተከሳሾች የቀረበባቸውን የሙስና ክስ ሙሉ በሙሉ አስተባብለዋል። በዲጂታል እና በሰነድ የተደገፉ ማስረጃዎችን የተቀበለው ፍርድ ቤቱም፣ ቀጣዩን የፍርድ ሂደት ለጁን 10 አስተላልፏል።

4 days ago