ሰላም፣ እንደምን አደራችሁ?
አብሮነት ለሀገር ግንባታና ለዘላቂ ልማት ከፍተኛ ሚና አለው፡፡
የሀገር ግንባታ የአንድን ማሕበረሰብ ሁለንተናዊ መዋቅር፣ የሕግ የበላይነትን፣ የኢኮኖሚ ጥንካሬንና የማህበራዊ ትስስርን በአንድ የጋራ ርዕይ ስር የመቅረጽ ዘላቂና ስልታዊ ሒደት ነው።
በታሪካዊና ባህላዊ እሴቶቿ የበለጸገችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በውጤታማ የሪፎርም ሒደትና በአስደናቂ የልማት ምዕራፍ ላይ ትገኛለች።
በዚህ ረገድ ሀገራዊ አንድነትና አብሮነት ለኢኮኖሚ እድገት ብሎም ለፖለቲካዊ መረጋጋት መሰረት ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ጊዜያት ባደረጓቸው ንግግሮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ላይ ልዩነቶች ሊኖሩ እንደማይገባ ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተደጋጋሚ እንዳሉት ፥ የልመናን ታሪክ በመቀየር ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገር ለመገንባት በሀገር ጉዳይ በአንድነት መቆም የግድ ይላል።
ለዚህም በፖለቲካና ሌሎች ጉዳዮች የሀሳብ ልዩነቶች ቢኖሩም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ለድርድር የሚቀርብ አለመሆኑን መገንዘብ እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት አብሮነት በማሕበረሰቡ መካከል እምነትንና ትብብርን በመገንባት ጠንካራ ማህበራዊ ካፒታል እንደሚፈጥር የሚያስገነዝብ ነው።
በዚህም በመንግሥት፣ በግል ባለሃብቱና በሕዝብ መካከል የተቀናጀ የልማት አጋርነት እንዲኖር በማስቻል ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ለማሳካት እንደሚያስችል ምስክር የሚሆኑ ሀገራዊ ስኬቶች ተመዝግበዋል።
የሀገር ግንባታ የተሟላ የሚሆነው አካታች በመሆን በሚከናወኑ ሀገራዊ ልማቶች የጥቂቶችን ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ዜጋ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ሲችል ብቻ ነው።
ኢትዮጵያ በጋራ ትገነባለች ምሁራንና ባለሙያዎች እውቀታቸውን ለሀገር ተቋማት ግንባታ ማዋል ይጠበቅባቸዋል።
ባለሃብቶች በልማት ስራዎች ላይ በስፋት ሲሰማሩ እንዲሁም አምራች ኃይል የሆነው ወጣት በፈጠራና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ በንቃት ሲሳተፍ፤ ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት መስክ በጋራ ለሀገር ጥቅም ሲተጋ ሀገር በጋራ ትገነባለች።
ኢትዮጵያን ወደ ላቀ የብልጽግና ምዕራፍ ማሸጋገር የሚቻለው ልዩነቶችን ወደ አዎንታዊ አቅም በመቀየርና የአብሮነት እሴቶችን በማጎልበት ብቻ ነው።
ስለዚህ ዛሬ የምናስቀምጠው የእውቀት፣ የጉልበትና የሀሳብ ጡብ ነገ ጠንካራና የማይናወጥ መንግሥታዊና ሀገራዊ መዋቅር ለመገንባት ያስችላል።
የጋራ ርዕይ፣ የጋራ ሥራና አብሮነት የኢትዮጵያ የወደፊት ጉዞ ስኬት ቁልፎች ናቸው።
ኑ ሀገር እንስራ!

7 days ago