በዓለ ኀምሳን በአንድነት ለማክበር የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ጥሪ አቀረቡ!
#fastmereja I የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ከአርሞኒየም ተሀድሶ ቤተክርስቲያን ጋር በመተባበር “ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን የዘንድሮውን የበዓለ ኀምሳ ቀን ሰኔ 7 እንደሚከበር በዛሬዉ እለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
ይህ ታሪካዊ የበዓለ ኀምሳ ቀን በዓል የፊታችን እሁድ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አዳራሽ በታላቅ ድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል።
የያሬድ መንገድ ተሀድሶ ቤተክርስቲያን መጋቢ የሆኑት ፓስተር ሄኖክ መንግስቱ በሰጡት ማብራሪያ፣ በዓሉ አማኞች በጋራ ሆነው መንፈስ ቅዱስን የሚያመሰግኑበትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ግንዛቤያቸውን የሚያሳድጉበት መሆኑን ገልጸዋል።
ፓስተር ሄኖክ አክለውም ቀደም ሲል በየግል ቤተክርስቲያኑ ይከበር የነበረው ይህ በዓል ዘንድሮ ግን በጋራና በአንድነት እንዲከበር መታቀዱን አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ተወካይ ፓስተር አሸብር ከተማ በበኩላቸው ይህ በዓል የአንድ ጊዜ ክስተት ወይም ስነ-ስርዓት (ceremony) ብቻ ሳይሆን፣ ዓመቱን ሙሉ ሊታሰብና ሊከበር የሚገባው ታላቅ በዓል ነው” ብለዋል።
የጥንቷ ቤተክርስቲያን በ24 ዓመታት ውስጥ መላውን ዓለም በወንጌል መድረስ የቻለችው በመንፈስ ቅዱስ መውረድ ምክንያት ባገኘችው መለኮታዊ ጉልበት መሆኑን የጠቀሱት ፓስተር አሸብር፣ በዓለ ሃምሳ የዶክትሪን ጉዳይ ሳይሆን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ቅድስናን እያወጁ የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋትና ወንጌልን በጋራ ለመስራት የሚተጉበት መሆኑን አስገንዝበዋል።
እሁድ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ በሚከበረው በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ መርሃ ግብር ላይ የእግዚአብሔር ቃል ስብከት፣ ልዩ የዝማሬና የአምልኮ ጊዜ እንዲሁም ስለ በዓለ ሃምሳ ትርጉምና አስፈላጊነት የሚያተኩር የውይይት መድረክ እንደሚኖር አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
እንዲሁም ካውንስሉ መላው የወንጌል አማኞች ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው በዓሉን በአንድነት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርቧል።

3 days ago