Logo
SeledaPost
በጉጂ ዞን አንዲት እናት 4 ልጆችን በሰላም ተገላገለች

በጉጂ ዞን በአዶላ ወዩ ሆስፒታል አንዲት እናት አራት ልጆችን በአንድ ጊዜ በሰላም መገላገሏ ተገልጿል ።
እናቲቱ  ከወሊድ ጊዜዋ አንድ ወር በፊት ጀምሮ ወደ አዶላ ወዩ ሆስፒታል በመምጣት የሕክምና ክትትል ታደርግ እንደነበር ተገልጿል።

በሕክምና ክትትል ላይ እያለች በዛሬው እለት ከ ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት 2 ወንድ እና 2 ሴት ሕፃናትን በሰላም መገላገሏን የማህፀንና ጽንስ ስፔሻሊስት ዶ/ር ሰሎሞን ከበታሙን በመጥቀስ  የጉጂ ዞን ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ዳንቆ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

እናቲቱና ሕፃናቱ በሙሉ በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እና ማንኛውም አስፈላጊ ድጋፍ ከሆስፒታሉ በኩል እየተደረገላቸው ይገኛል።
መረጃው የ ዳጉ ጆርናል ነው

Seledadotio
Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.