Logo
FastMereja
በኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ ተመረቀ።

በአይናለም አዱኛ (ዶ/ር) የተጻፈውና በኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ ላይ ትኩረቱን ያደረገው "Walking Between Worlds: Letter to the Next Generation of the Ethiopian Diaspora" የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።

በትናንትናው ዕለት በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ሲመረቅም የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ፣የአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶር ሳሙኤል ክፍሌን ጨምሮ ምሑራን ዲያስፖራዎችና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። ስለኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ በምሁራንና በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
በአሜሪካ ሀገር ካሊፎርንያ ግዛት ኑሯቸውን ያደረጉት ዓይናለም አዱኛ(ዶ/ር) ከ38 ዓመታት በላይ ኖረዋል።

መጽሐፉ በውጭ የውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ልጆቻቸው ስለሀገራቸው እንዲያውቁ እና የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

በውጭ ሀገር የነበራቸውን የረጅም ጊዜ ልምድና ገጠመኝ በመነሳት እንደጻፉትና ለሌሎች ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን አስተማሪ ታሪኮችን የያዘ ስለመሆኑ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ በዚህ ወቅት እንዳሉትም በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ሀገራት እንደሚኖሩ ገልጸው በሀገራቸው ሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት እየተሳተፉ ይገኛል።
ዶር ዓይናለም አዱኛ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምሳሌ የሚሆን ተግባር መስራታቸውን በመግለጽ ይህ በጎ ተግባር መቀጠል አለብ ብለዋል።
መጽሐፉ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለንባብ የበቃ ሲሆን 480 ገጽ ያለው ነው።

6 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.