ምክክሩ ለጠንካራ ሀገራዊ አንድነት ወሳኝነት አለው
***************
የሀገራዊ ምክክር መድረኮች የሀሳብ ልዩነቶች የክፍፍል ምንጭ ከመሆን ይልቅ ለሀገር ግንባታ የሚጠቅሙ የጎለመሱ አማራጮች የሚወለዱባቸው አውዶች ናቸው።
ምክክር ማዳመጥን፣ መከባበርንና የጋራ መግባባትን መሰረት ያደረገ በመሆኑ በልዩነቶች መካከል ድልድይ የመገንባት አቅም አለው።
በተለይም ወቅቱ የሚጠይቀውን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የተለያዩ ፍላጎቶችና ድምፆች ያካተተ ውይይት ማድረግ ወሳኝ ነው።
እውነተኛና ግልጽ ምክክር ጥርጣሬዎችን አስወግዶ መተማመንን በመፍጠር ረገድ የሚተካው የለም።
ዘላቂ ሰላምን የማስፈን ሒደትም የተለያዩ አካላትን ንቁ ተሳትፎና በቅን ልቦና የመወያየት ቁርጠኝነትን ይጠይቃል።
ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ ስኬታማ ለማድረግና ልዩነቶቻችንን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያከናወናቸው ያሉትን ሥራዎች በሁሉም አቅጣጫ መደገፍ ይገባል።
በመሆኑም ይበልጥ በዕድገት ጎዳና ለመራመድ፣ ያለፉ ስህተቶችን አርሞ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር እና ጠንካራ አንድነት ለመገንባት ሁላችንም ለምክክር ባህል ቅድሚያ መስጠት ይኖርብናል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #national #dialogue

11 days ago