በአዲስ አበባ የፈጣን አውቶቢስ ትራንስፖርት ኮሪደር ግንባታ በጥሩ ፍጥነት ላይ እንደሚገኝ ተነገረ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ ከጎፋ ማዞሪያ ተነስቶ በሜክሲኮ በኩል እስከ ፒያሳ የሚዘልቀው የፈጣን አውቶቢስ መስመር (BRT B2) ኮሪደር የልማት ፕሮጀክት ግንባታ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑ ታውቋል።
በፈረንሳይ የልማት ድርጅት እና በከተማዋ አስተዳደር በጋራ የገንዘብ ድጋፍ የሚከናወነውን የዚሁ የመጀመሪያ ምዕራፍ የሙከራ ፕሮጀክት ግንባታ የቻይናው ኮሚኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ እያካሄደው ሲሆን፣ ሲስተራ የተባለው ተቋም ከኮር አማካሪ ድርጅት ጋር በመሆን የማማከርና የቁጥጥር ስራውን እያከናወኑት ይገኛሉ።
በአሁኑ ሰዓት ከቡልጋሪያ ማዞሪያ እስከ ገነት ሆቴል ባለው ወደ አንድ ኪሎ ሜትር ገደማ በሚጠጋው መንገድ ላይ የአፈር ቆረጣ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ዝርጋታ፣ የከልቨርት ቦክስ ግንባታና የሙሌት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ይህ ስምንት ነጥብ ሁለት ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የመጀመሪያ ምዕራፍ ፕሮጀክት በተጠናከረ ሁኔታ እየቀጠለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ከጎፋ እስከ ጀሞ መብራት የሚዘልቀውን ሁለተኛውን ምዕራፍ ግንባታ ለመጀመር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው።
ቀደም ሲል ከጀሞ ሚካኤል ትራፊክ መብራት እስከ ጀሞ ሶስት አደባባይ ያለው መስመር በአስፋልት ንጣፍ ተጠናቆ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ይህ አዲሱ የፈጣን አውቶቢስ ኮሪደር ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ የከተማዋን የህዝብ ትራንስፖርት ችግር በከፍተኛ ደረጃ ያቃልላል ተብሎ ይጠበቃል።
#አዲስአበባ #ትራንስፖርት #የመንገድግንባታ #brt #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

6 days ago