Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር በአልጄሪያ ሄንሪ ኤንሸር፣ የአሜሪካ አስተዳደር እስራኤል በደቡብ ሊባኖስ የምታካሂደውን ጥቃት በተመለከተ "ነጻ እጅ" (ማንኛውንም ነገር የመወሰንና የመፈጸም ነጻነት) እንደሰጣት ገለጹ።

አምባሳደሩ ለአልጄዚራ እንደተናገሩት የአሜሪካ በሊባኖስ ያላት ብሔራዊ ጥቅም በዋናነት የሚገለጸው በቤሩት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በማስቆም ላይ ብቻ እንጂ፣ ከዋና ከተማዋ ውጭ በሚደረጉ ወታደራዊ እርምጃዎች ላይ አይደለም። "የአሜሪካ አስተዳደር ለእስራኤል በደቡብ ሊባኖስ ቢያንስ ለአሁኑ ጊዜ ነጻ እጅ መስጠቱ ግልጽ ነው" ሲሉ አምባሳደሩ አስረድተዋል።

ሄንሪ ኤንሸር አክለውም ሄዝቦላህ በደቡብ ሊባኖስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ከሰነዘረ እና እስራኤልም በምላሹ እዚያው አካባቢ እንዲሁም ወደ ሰሜን እስራኤል በሚደርሱ የሄዝቦላህ ጥቃቶች ላይ እርምጃ ከወሰደች፣ የአሜሪካ አስተዳደር ይህንን ሁኔታ "ተቀብሎ ለመኖር" ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አስተያየት የአሜሪካን አቋም ከቤሩት ደህንነት ጋር በማያያዝ፣ በደቡብ ሊባኖስ እየተካሄደ ላለው የእስራኤል ወታደራዊ እርምጃ እውቅና የሰጠ አካሄድ መሆኑን ያሳያል።

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.