የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ፤ በ"ቪቫ ሶፍት" ላይ ተፈጽሟል በተባለ "የንግድ ምልክት መብት ጥሰት ወንጀል" የጠረጠራቸውን አቶ ሰይድ መሐመድኑር ዑመርን በቁጥጥር አውሎ ምርመራ ጀምሯል።
ፖሊስ ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ወንጀል ችሎት ባቀረበው ማመልከቻ መሠረት፣ "ፒዩር ዉድ ፐልፕ ኤንድ ፔፐር ፓኬጂንግ" ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ሕጋዊ የምዝገባ ሰርተፍኬት ቁጥር LTM/3249/2017 የተሰጠውንና በዓለም አቀፍ ምድብ 16 ሥር የሚገኘውን የ"VIVa" (ቪቫ ሶፍት) የንግድ ምልክት ተጠርጣሪው ያለ ባለቤቱ ዕውቅና እና ፈቃድ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል። ተጠርጣሪው ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የቪቫ ሶፍትን ማሸጊያ ፕላስቲክ ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ አመሳስለው በመሥራት፣ ጥራቱን ያልጠበቀ ምርት ገበያ ላይ ሲያሰራጩ እንደነበር በጥቆማ ደርሶኛል ብሏል - ለፍርድ ቤቱ።
ይህ ጥራቱን ያልጠበቀ፣ ጤናማ ያልሆነ ኬሚካል እንዲሁም ተረፈ ምርት ጥቅም ላይ የዋለበት ፎርጅድ የሶፍት ምርት በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች በድብቅ እንዲሰራጭ መደረጉን የገለጸው ፖሊስ፣ ድርጊቱ ሸማቹን የማታለልና ህገ ወጥ ተግባር መሆኑን ለፍርድ ቤቱ ጠቅሷል። በተጨማሪም ድርጊቱ ጤናማ የገበያ ውድድርን የሚያዛባ፣ መንግስት ማግኘት ያለበትን የታክስ ግብር የሚያሳጣና በኢኮኖሚው ላይ ቀውስ ለመፍጠር ሆን ተብሎ የተፈጸመ ውስብስብ ወንጀል መሆኑን በማመልከቻው አስረድቷል።
ተጠርጣሪው ከእስር ቢወጡ ማስረጃዎችን ሊያጠፉ፣ ይዘት ሊቀይሩና ምስክሮችን ሊያባብሉ ስለሚችሉ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በሰነድ አሟልቶ ለመጨረስ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ እንዲሰጠው ፖሊስ ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ነበር።
ፍርድ ቤቱም ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት የፖሊስን ጥያቄ መርምሮ የ7 ቀናት የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ የፈቀደ ሲሆን፣ በቀጣይ የምርመራ ውጤት ለመስማት ለሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

4 hours ago