ቅዱስ አማኑኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ በሐጢዓት ፈተና ተጠልፎ ከመውደቅም ይጠብቀን🙏
አማኑኤል ‹አማነ› እና ‹ኤል› ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው፤ ትርጓሜውም የአምላክ ሰላም፣ የእግዚአብሔር እርቅ፣ የጌታ አንድነት ማለት ነው። አማኑኤል ማለት እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ደግሞ ከሥጋችን ሥጋ ከነፍሳችን ነፍስ ነሥቶ የተዋሐደ ከብቻዋ ከኃጢአት በቀር እንደኛ የሆነ ማለት ነው። አዳም ዕፀ በለስን በልቶ የሞት ፍርድ በተፈረደበት ጊዜ አምላኩ እግዚአብሔር እዲያድነው ስለተማጸነው በርኅራኄው ወደ ቀድሞ ቦታው እንደሚመልሰው በሰጠው ተስፋ ከልጅ ልጁ ተወለዶ አዳነው፡፡ በዚያችም በተከበረች ቀን ትንቢቱ ተፍጽሞ አምላካችን ከእኛ ጋር ሆነ፡፡
አንድም “ይህ ዐማኑኤል የተባለ ስም እጅግ ታላቅ ስም ነው፣ የማይለይ ተዋሕዶን የሚገልጽ የሃይማኖት መሠረት ነው” ይሉናል፡፡ “ዒማኑ” ማለት ምስሌነ ከእኛ ጋር ማለት ሲሆን፣ “ኤል” አምላክ በተገናኘ፣ አምላክ ምስሌነ ወይም ምስሌነ አምላክ፣ አምላክ ከኛ ጋራ ማለት እንደሆነ በኢሳይያስ 7÷14፣ በማቴዎስ 1÷23 ተጽፏል፡፡ ሊቃውንት ግን “አምላክና ሰው” ወይም ሰው የሆነ አምላክ፣ በመለኮቱ አምላክ፣ በለበሰው ስጋም ሰው ብለው በምስጢር ይፈቱታል፡፡ አምላክ ሰው የሆነለት የሰው ልጅ ኃጢአት ተፋቀ፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ “እነሆ ድንግል በድንግልና ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች” ብሎ እንደተናገረው እግዚአብሔር ወልድ ከንጽሕተ ንጹሐን ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ተወለደ፡፡ ገዳማውያን እናቶችና አባቶች ይህን ስም መመኪያ አድርገው ነው ዓለምን ንቀው የመነኑት፡፡ እርሱ ከኛ ጋር ከሆነ እኛ ከዓለም ጋር ምን ሕብረት አለን ብለው የምንኩስናን ጎዳና መረጡ ገዳማቸውን ስንደግፍ አዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

1 day ago