(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዶናልድ ትራምፕ በሚኒሶታ ስለተፈጠረው ማጭበርበር የሐሰት ወሬ በማሰራጨት "እጅግ ብልሹ" ሲሉ እንደወነጀሏቸው የገለጹት የኮንግረስ አባል ኢልሃን ዑመር፣ ይህ ድርጊት የትራምፕ የራሳቸው ውድቀቶች እና ሙስናዎች ሲጋለጡባቸው በእሳቸው እና በሶማሌ ማኅበረሰብ ላይ ጥላቻን ለመቀስቀስ የሚጠቀሙበት የተለመደ ስልት መሆኑን አስታውቀዋል። አቅጣጫን የማስቀየር፣ የዘረኝነት እና የውሸት ፖለቲካ የትራምፕ ዋነኛ መገለጫ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ይህ የትራምፕ አካሄድ አዲስ ስልት እንዳልሆነ ያነሱት ኢልሃን ዑመር፣ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሊንደን ቢ ጆንሰንን ጠቅሰዋል። ፕሬዚዳንቱ በወቅቱ እንዳሉት አንድን ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያለ ነጭ ሰው ከምርጥ ጥቁር ሰው እንደሚበልጥ ማሳመን ከተቻለ፣ ኪሱ ሲዘረፍ እንኳ አያስተውልም፤ እንዲያውም የሚንቀው ሰው ከተሰጠው የራሱን ኪስ አራግፎ ይሰጣል ብለው ነበር። ኢልሃን ዑመር ይህንኑ ንግግር በማስታወስ፣ ትራምፕ ጥቁሮችን እና ነጮች ያልሆኑ ማኅበረሰቦችን በማንቋሸሽ ሕዝቡ እሱ ራሱ በጠራራ ፀሐይ የሀገር ሀብት ሲመዘብር እንዳያስተውል እያደረገ ይገኛል ብለዋል። ማጭበርበርን እንደ ፖለቲካዊ መሣሪያ እየተጠቀመ የራሱን የገንዘብ ደጋፊዎች እንደሚጠብቅ እና ራሱን እንደሚያበለጽግም ተችተዋል።
ትራምፕ ማጭበርበርን ስለመከላከል ምንም ደንታ እንደሌለው የገለጹት የምክር ቤት አባሏ፣ በተቃራኒው በጤና አጠባበቅ እና በባንክ ዘርፍ በሚሊዮኖች እና በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ያጭበረበሩ እና የተፈረደባቸውን ግለሰቦች በይቅርታ እንደለቀቀ አጋልጠዋል። ከነዚህም መካከል በጤና ዘርፍ ታይቶ የማይታወቅ ማጭበርበር የፈጸሙ እና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የዘረፉ ታላላቅ ወንጀለኞች ይገኙበታል። አሁን ደግሞ በጥር 6ቱ የካፒቶል ሁከት ፖሊሶችን ለደበደቡ እና ሕንጻውን ላወደሙ ግለሰቦች የካሳ ክፍያ የሚሆን እጅግ ግዙፍ ፈንድ ከሕዝብ ግብር በመመደብ አሜሪካውያንን በድጋሚ እያጭበረበረ መሆኑን አብራርተዋል።
ማጭበርበር የትም ይከሰት የት መወገድ እንዳለበት ያመላከቱት ኢልሃን ዑመር፣ ሕፃናትን ለመመገብ የተመደበን በጀት ያጭበረበሩ ግለሰቦች ያለ ምንም ልዩነት በሕግ ሊጠየቁ ይገባል ብለዋል። በልጅነታቸው በስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ የረሃብን ስቃይ እንዳሳለፉ በማስታወስ፣ የራሳቸውን ልጆች የሚመግቡት አጥተው ሲራቡ ማየት ለወላጆች ምን ያህል አሳዛኝ እንደሆነ በሚገባ እንደሚረዱ ገልጸዋል። በመሆኑም ሕፃናትን ከረሃብ ለመታደግ የተቋቋመን ፕሮግራም በግል ጥቅም መበዝበዝ እጅግ አሳፋሪ እና ጸያፍ ተግባር መሆኑን በመጥቀስ፣ ወንጀሉ ሲጋለጥ ጀምሮ ፈጻሚዎቹ ለሕግ እንዲቀርቡ ጠንካራ ጥያቄ ሲያቀርቡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።
ሚኒሶታ ውስጥ የተፈጸመውን ይህንን ወንጀል የፖለቲካ ትርፍ ማግኛ ካደረጉት ትራምፕ እና ሪፐብሊካኖች በተቃራኒ፣ የሚኒሶታ አመራሮች አጭበርባሪዎቹን ለሕግ በማቅረብ ረጅም የእስር ቅጣት እንዲተላለፍባቸው ማድረጋቸውን ጠቁመዋል። ትራምፕ ሌቦችን ከእስር ሲለቅ፣ የክልሉ አመራሮች ግን እውነተኛ ተጠያቂነትን በተግባር በማሳየት ወንጀለኞችን ከርቸሌ አውርደዋል ብለዋል።
የትራምፕ ቤተሰብ ከዘመናዊ የዲጂታል ገንዘብ ግብይት ትርፍ እያጋበሰ እና የፕሬዚዳንትነት ሥልጣን ለሽያጭ የቀረበ እስኪመስል ድረስ የግል ብልጽግናን እያሳደደ መሆኑን የጠቀሱት ዑመር፣ የትራምፕ ዩኒቨርሲቲን ማጭበርበር እና የበጎ አድራጎት ተቋሙን ሕገ-ወጥ አሠራር በምሳሌነት አንስተዋል። በመጨረሻም፣ ትራምፕ የራሱን ሙስና ለመሸፈን ዘረኛ የሆኑ የፈጠራ ወሬዎችን እንደሚያሰራጭ በመግለጽ፣ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ እንዳሱ ያለ ታላቅ አጭበርባሪ ታይቶ አያውቅም ሲሉ ጽሑፋቸውን ቋጭተዋል።

11 days ago