Logo
EBC
እስካሁን ያላባራው የአሜሪካ እና የኢራን ውዝግብ
******************

በአሜሪካ፣ እስራኤል እና ኢራን መካከል ስላለው የተኩስ አቁም ድርድር እርስ በርሱ የሚጋጭ መረጃ እየወጣ ነው።

ከኢራን አብዮታዊ ዘብ (IRGC) ጋር ቅርበት ያላቸው የኢራን የዜና ወኪሎች ፋርስ እና ተስኒም፣ ኢራን ከተኩስ አቁም አደራዳሪዎች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ማቋረጧን ዘግበዋል።

ኢራን በሊባኖስ (በእስራኤል እና በሂዝቦላህ መካከል) ያለው ግጭት ካልቆመ በስተቀር ድርድሩ እንደማይቀጥል ገልጻለች።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን “ሀሰት” ሲሉ ይህን ዘገባ አስተባብለዋል። "ንግግሩ ትናንትም ዛሬም ያለማቋረጥ እንደቀጠለ ነው፤ ኢራን ስምምነት ላይ የምትደርስበት ጊዜው አሁን ነው" ብለዋል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ስለ ግንኙነቱ መቋረጥ የተባለውን ባያረጋግጡም፣ ስለ ኑክሌር ድርድሩ ሂደት ግን ተስፋ ሰጪ ሁኔታዎች እንዳሉ ጠቁመዋል።

ኢራን በሆርሙዝ የንግድ መስመር ላይ ያላትን ስትራቴጂያዊ የበላይነት በመጠቀም፣ አሜሪካ እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት እንድታስቆም እየጠየቀች ትገኛለች።
#middleeast #iran #usa #trump

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.