Logo
EBC
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለው የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ መርቀው ሥራ አስጀመሩ
**********************

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት፣ ዛሬ ጠዋት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት መርቀው በይፋ ሥራ ማስጀመራቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ ‎ይህ ትልቅ ተነሣሽነት፤ የተራቆቱ አካባቢዎችን በዘመናዊ የአፈር ጥበቃ እና በወንዝ ማጣራት ወደ አረንጓዴ ስፍራዎች በመቀየር፣ የፍራፍሬ ፓርኮችን ከእግር ጉዞ እና ከብስክሌት መንገዶች ጋር በማቀናጀት መዲናችንን አድሷል ብለዋል።

‎በአጠቃላይ 22.25 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማትን የሚሸፍነው ይህ ፕሮጀክት፣ የማይቆራረጥ የልማት ሥራችን ሕያው ምስክር ከመሆኑም በላይ የሀገራዊ ዕድገታችን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የከተማ እድሳት በተግባር የታየበት ነው ሲሉም አክለዋል።
#ebc #ethiopia #pmabiyahmed #development

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.