በምዕራብ ሸዋ ዞን የምርጫው ሂደት ያለምንም ተፅዕኖ በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን የኦነግ ተወካይ ገለጹ
******************
በምዕራብ ሸዋ ዞን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ተንቀሳቃሽ ታዛቢና ተወካይ ሚልኬሳ ኢርኮ ጊዲ፣ ከጠዋት ጀምሮ በከተማዋ ያሉትን ሁሉንም የምርጫ ጣቢያዎችና እስከ ጎሱ ቆራ ወረዳ ድረስ በመዘዋወር ሂደቱን ሲከታተሉ መቆየታቸውን አስታውቀዋል፡፡
ተወካዩ እንደገለጹት፤ ሕዝቡ በጥሩ ሁኔታና ያለምንም ተፅዕኖ ድምፁን ሰጥቶ እየሄደ ይገኛል፡፡
በዘንድሮው ምርጫ ተወዳዳሪዎች ከየትኛውም ጊዜ በላይ በከፍተኛ ሁኔታ መሳተፋቸውንና ድርጅታቸው ኦነግም በሂደቱ ላይ መካተቱን ጠቅሰው፣ ያጋጠመ ምንም ዓይነት እንቅፋት እንደሌለ አስገንዝበዋል፡፡
የምርጫው ፍጻሜም አሁን እየሄደበት ባለው መልኩ መልካም ከሆነ ሁሉም ፓርቲዎች በዴሞክራሲያዊ መንገድ የፈለጉትን እንደሚያገኙና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ በስምምነት መሥራት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
በበረከት ሽመልስ

5 days ago