Logo
EBC
አስከሬን በቤት አስቀምጠው ለምርጫ የወጡት የቤተሰብ አባላት - የላቀ የዜግነት ቁርጠኝነት ተምሳሌት!
*************

በሰሜን ሽዋ ዞን ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ፣ አባያ ቀበሌ (ሳክላ ምርጫ ጣቢያ) እጅግ ልብ የሚነካ እና ታላቅ የዜግነት ኃላፊነት የታየበት ክሥተት ተመዝግቧል።

ልጃቸው በሞት የተለየባቸው ቤተሰቦች፣ አስከሬን በቤት አስቀምጠው 7 የቤተሰቡ አባላት በማለዳ ወደ ምርጫ ጣቢያ አምርተዋል። በቦታው የነበረው ማኅበረሰብም ለኀዘናቸው ጥልቅ ክብር በመስጠት፤ ሰልፍ ሳይጠብቁ ቅድሚያ ሰጥተዋቸው ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ ወደ ልቅሶ ቤታቸው ተመልሰዋል።

ይህ ተግባር ሕዝባችን በምርጫው ሂደት ላይ ያለውን ጽኑ እምነት እና ለሀገሩ ያለውን የላቀ ክብር በተግባር ያረጋገጠበት ህያው ምስክር ነው ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ናቸው።

Ethiopian Broadcasting Corporation #ምርጫ #አማራ #ክልል

3 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.