Logo
SeledaPost
#የህፃናት ማጅራት ገትር #በሽታ (#meningitis) ምንድነው❓️

📝 የማጅራት ገትር ህመም ወይንም በህክምናው አጠራር ሜኔንጃይትስ(Meningitis) የምንለው አንጎልን እና ህብረሰረሰርን ሸፍኖ የሚገኝ የሰውነታችን ክፍል በኢንፌክሽን ሲጠቃ ነው።

📝 የማጅራት ገትር በሽታ በቫይረስ፣በባክቴሪያ ወይንም በፈንገስ ምክንያት ሊከሰት ይችላል።

✏️ ይህ ህመም በአፋጣኝ ህክምና ካልተደረገለት ለከፍተኛ ጉዳት ከዚያም ባለፈ ለህልፈተ ህይወት ሊዳርግ የሚችል ነው።

👉 #ለማጅራት ገትር #ህመም ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው?

✔️ የጆሮ እና የሳይነስ ኢንፌክሽን
✔️ የጭንቅላት በአደጋ መጎዳት
✔️ የእናት ጡት ወተት ጠብቶ አለማደግ
✔️ ክትባት አለመከትብ
✔️ ዝቅተኛ የበሽታ የመከላከል አቅም
✔️ ተጠጋግቶ መኖር
✔️ ኤች አይ ቪ ቫይረስ
✔️ የስኳር ህመም

👉 የማጅራት ገትር ህመም ምልክቶች ምንድንናቸው?

✏️ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት
✏️ የአንገት ህመም
✏️  ከፍተኛ የሆነ የራስምታት
✏️ ማቅለሽለሽና ትውከት (ማስመለስ)
✏️ እራስን መሳት
✏️ ማንቀጥቀጥ
✏️ግራ መጋባት እና ትኩረት ማጣት
✏️ ብርሃን መፍራት
✏️ የምግብ ፍላጎት መቀነስ

📝 አንድ ህፃን ልጅ ሳይታከም ከበሽታው ጋር የሚቆይ ከሆነ  ዉሎ አድሮ ብዙ አይነት የጤና መዘዞች ችግሮች ሊኖሩት ይቺላል ለምሳሌ

✏️የሚጥል በሽታ
✏️ የመስማት ችሎታን ማጣት
✏️የማስታዎስ ችግር
✏️ የመማር ብቃትን ማጣት
✏️ ሚዛን ጠብቆ የመቆም እና የመራመድ ችግር
✏️የኩላሊት ህመም እና የመሳሰሉት ናቸው።
✔️ ተገቢውን ህክምና በአፋጣኝ የሚያገኝ ከሆነ ግን ከህመሙ በሚገባ ሊያግግም ይችላል።

Seledadotio
Seledadotio
4 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.