(ዘ-ሐበሻ መዝናኛ) ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በ'ፍሪደም 250' ታላቁ የአሜሪካ ስቴት ፌር ላይ አንዘፍንም ብለው ፊታቸውን ባዞሩ አርቲስቶች ላይ በቁጣ ገንፍለዋል፤ አልፎ ተርፎም ይህን ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ሊያሰርዙት ቋምጠዋል!
47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በ'ትሩዝ ሶሻል' ገጻቸው ላይ በለቀቁት ቦምብ መሳይ መልእክት፣ አርቲስቶቹን "ማንም ሊሰማቸው የማይፈልግ፣ ሙዚቃቸው አሰልቺ የሆነ፣ ነገር ግን ከማማረር ውጪ ምንም የማያውቁ ውድ ዘፋኞች" በማለት ክፉኛ ዘልፈዋቸዋል።
ትራምፕ ቁጣቸው በዚህ ብቻ አላበቃም፤ አሜሪካ ነጻ የወጣችበትን 20ኛ ዓመት በዓል ተከትሎ የሚዘጋጀው የ'ፍሪደም 250' ዝግጅት በአስቸኳይ እንዲሰረዝ በመጠየቅ፣ ዝግጅቱን "ከመፈራረስ አፋፍ ላይ ከሚገኘውና ደህንነቱ አስተማማኝ ካልሆነው የኬኔዲ ሴንተር" ጋር አመሳስለውታል።
እንደሚታወቀው ትራምፕ ሰኔ 24 በዋሽንግተን ዲ.ሲ. 'ናሽናል ሞል' ለአሜሪካ 250ኛ ዓመት የልደት በዓል ማድመቂያ የሚሆነውንና በ'ፍሪደም 250' አዘጋጅነት የሚካሄደውን ይህን ታላቅ ዝግጅት በይፋ ይከፍታሉ ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ለዚሁ ዝግጅት በርካታ ታዋቂ ሙዚቀኞች ተጠርተው የነበረ ቢሆንም፣ ጥቂቶቹ ግን በድንገት እግራቸውን አውጥተዋል። ከነዚህም መካከል 'ዘ ኮሞዶርስ'፣ ማርቲና ማክብራይድ፣ ሞሪስ ዴይ እና ዘ ታይም፣ የ'ፖይዘን'ው ድምጻዊ ብሬት ማይክልስ፣ እንዲሁም ራፐሩ ያንግ ኤምሲ ይገኙበታል።
እነዚህ አርቲስቶች ከዝግጅቱ ራሳቸውን ያገለሉበትን ምክንያት ሲያስረዱ "ዝግጅቱ ከማንኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዳ ነው ተብለን ተዋሽተናል፤ እውነታው ግን ፈጽሞ የተለየ ነው" ብለዋል። ለነገሩ ትራምፕ 'ፍሪደም 250'ን ባለፈው አመት ያስጀመሩት ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት ዝግጅቱን በዋናነት እየመሩት ያሉት የቀድሞው የትራምፕ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ተሿሚ የሆኑት ኪዝ ክራች ናቸው።
ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ተስፋ አልተቆረጠም! ዝግጅቱ ሙሉ በሙሉ ገደል ካልገባ በስተቀር... ፍሎ ራይዳ፣ ቫኒላ አይስ እና ፍሪደም ዊሊያምስ መድረኩን በሙዚቃዎቻቸው ለማንቀጥቀጥ አሁንም ዝግጁ ናቸው።
ወደ ኬኔዲ ሴንተር ውዝግብ ስንመለስ ትራምፕ በታሪካዊው የኪነ-ጥበብ ማዕከል ላይ ሊያደርጉት የነበረውን እድሳት በቅርቡ ባገዱባቸው የፌደራል ዳኛ ላይ አሁንም እሳት እየተፉ ነው።
ዳኛው አርብ እለት ባሳለፉት ውሳኔ ፕሬዚዳንቱ "ትራምፕ ኬኔዲ ማዕከል ሊሉት" ፈልገው የነበረ ሲሆን፤ የትራምፕ ስም ከማዕከሉ ሙሉ በሙሉ እንዲፋቅ ማዘዛቸው ይታወሳል። ይህ ውሳኔ ያንገበገባቸው ትራምፕም፣ በ'ትሩዝ ሶሻል' ገጻቸው ላይ ዳኛውን “ጸረ-ትራምፕ እና በጥላቻ ያበዱ” ሲሉ ያብጠለጠሏቸው ሲሆን፣ ታሪካዊውን የኬኔዲ ሴንተር ደግሞ "በሞት አፋፍ ላይ ያለ" በማለት ክፉኛ ተችተውታል!

5 days ago