Logo
FastMereja
የአይኤምኤፍ (IMF) የብር ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ በገበያ እንዲወሰንና ድጎማዎች እንዲነሱ ጠየቀ

​#fastmereja I የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ልዑክ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ላይ ያደረገውን አምስተኛ ግምገማ በአዲስ አበባ አጠናቋል። ድርጅቱ የኢትዮጵያ መንግስት የብርን የውጭ ምንዛሬ ተመን ሙሉ በሙሉ ለገበያ ፍላጎትና አቅርቦት እንዲተው፣ የመንግስት ቀጥተኛ ድጎማዎችን በሂደት እንዲያስወግድ እና የሀገር ውስጥ ታክስ ስብሰባን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያሳድግ ጠይቋል።

​ይህ የአይኤምኤፍ ጥያቄ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን ተከትሎ፣ ውሳኔው በተራው ህዝብ እና በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ፈጣንና ከፍተኛ ጫና እያሳደረ ይገኛል። የብር የመግዛት አቅም መውረድ፣ የዋጋ ንረት መናር እና የኑሮ ውድነት መባባስ ዋነኛ ማሳያዎች ናቸው።

በተጨማሪም መንግስት የታክስ ገቢውን ለማሳደግ የጀመረው ጥብቅ ቁጥጥር፣ መደበኛውን የታክስ ህግ የማስከበር ሂደት ወደ አስገዳጅ የቀየረው ይመስላል ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል።

​ምንም እንኳን ማሻሻያው የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ መረጋጋትን ያመጣል ተብሎ በዓለም አቀፍ ተቋማት ቢታመንም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ግን ማህበረሰቡን እና የግሉን ዘርፍ ክፉኛ እየፈተነ ይገኛል። መንግስት በበኩሉ የድሆችን ጫና ለመቀነስ የማህበራዊ ደህንነት መረቦችን እንደሚዘረጋ ቀደም ሲል መግለጹ ይታወሳል።

ዘገባው የአዲስ ፎርቹን ነው።

10 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.