"ቲፕ" ታገኛላችሁ በሚል በአነስተኛ ክፍያ የሚሰሩትን የመስተንግዶ ሰራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ወደ 5ሺህ ብር ከፍ ለማድረግ እንደሚሰራ ማኅበሩ አስታወቀ
በቅርቡ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ ይካሔዳል ተብሏል፡፡
በኢትዮጵያ በሆቴል መስተንግዶ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎች ከደንበኞች ተጨማሪ የማበረታቻ ጉርሻ ወይም "ቲፕ" ያገኛሉ በሚል የአሠሪዎች የተሳሳተ ግምት ምክንያት ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና መጋለጣቸውን የኢትዮጵያ መስተንግዶ ባለሞያዎች ማኅበር ለአሐዱ አስታውቋል።
ማኅበሩ ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር መፍትሔ ለማሰጠት እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።
የመስተንግዶ የባለሙያዎችን አነስተኛ የደመወዝ ወለል ወደ 5 ሺህ ብር ከፍ ለማስደረግ የደብዳቤ ልውውጥና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ማኅበሩ ገልጿል።
የማኅበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ያሬድ ደገፉ፤ "አሠሪዎች እና ማኅበረሰቡ የመስተንግዶ ባለሙያዎች የተሻለ ተጨማሪ ገቢ ያገኛሉ የሚል የተሳሳተ አመለካከት አላቸው" ብለዋል።
አቶ ያሬድ በተጨማሪም "ቲፕ" በተገልጋዩ ፈቃደኝነት እንዲሁም በእድል እና አጋጣሚ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ለሠራተኛው ቋሚ የኑሮ ዋስትና ሊሆን አልቻለም ብለዋል።
አንዳንድ አሠሪዎች ቲፕን ከተቋሙ የሚገኝ ገቢ በማስመሰል እንደ መደራደሪያ በማቅረብ የባለሙያዎችን መብትና ጉልበት ዝቅ አድርገው እንደሚመለከቱ ፕሬዝዳንቱ አስረድተዋል።
ከደንበኞች የሚሰበሰበው የአገልግሎት ክፍያ (ሰርቪስ ቻርጅ) ከሠራተኛው ደመወዝ ጋር ተጨምሮ መከፈል ሲገባው አብዛኛዎቹ ሆቴል እና ሬስቶራንቶች ይህንን ባለማድረጋቸው ሠራተኛው እየተጎዳ እንደሆነም ተነስቷል።
በአሁኑ ወቅት በሥራ በሚበዛባቸው ሆቴሎች ጭምር ለአንድ የመስተንግዶ ባለሙያ የሚከፈለው ከፍተኛው የወር ደመወዝ 3 ሺህ ብር ብቻ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ያሬድ፣ በዚህም ምክንያት ባለሙያዎቹ ሕይወታቸውን ለመምራት በቀን ከ8 ሰዓት መደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ በሁለትና በሦስት ቦታዎች እስከ ምሽቱ 3:00 ድረስ በከፍተኛ ድካም ተጨማሪ ሥራ ለመሥራት መገደዳቸውን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት መንግሥት አነስተኛ የደመወዝ ወለል 5,000 ብር እንዲሆን ባስቀመጠው ጭብጥ መሠረት፣ ይህንን ተፈጻሚ ለማድረግ ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከአሠሪዎች ፌዴሬሽን እንዲሁም ከግሎባል ሠራተኞች ማኅበር ጋር ውይይቶች እየተደረጉ ነው ተብሏል።
የመስተንግዶ ሰራተኞች ደሞዝ እና ጥቅማ ጥቅም በሕግጋዊ ማዕቀፍ እንዲደገፍና ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጠው በማሰብም በቅርቡ ትልቅ ሀገራዊ ኮንፈረንስ ለማዘጋጀት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል።
#አሐዱ

13 days ago