(ዘ-ሐበሻ ዜና) በዋይት ሃውስ አቅራቢያ የተኩስ ድምፅ መሰማቱ ተገለጠ
ቅዳሜ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የዋይት ሃውስ ሰሜናዊ ሜዳ አቅራቢያ የተኩስ ድምፅ መስተጋባቱን የሲቢኤስ ኒውስ ጋዜጠኞች ዘግበዋል።
ከምሽቱ 6 ሰዓት በኋላ ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ 20 የሚጠጉ የተኩስ ድምፆች የተሰሙ ሲሆን፥ ድምፁ የመጣው የኢዘንሃወር አስፈፃሚ ቢሮ ህንፃ ከሚገኝበት የዋይት ሃውስ ቅጥር ግቢ አቅጣጫ መሆኑ ተነግሯል።
ክስተቱን ተከትሎ የአሜሪካ ሚስጥራዊ ጥበቃ አገልግሎት በቦታው የነበሩ የብዙሃን መገናኛ አባላትን በፍጥነት ወደ ዋይት ሃውስ የውስጥ ክፍል እንዲገቡ አድርጓል።
የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ስቲቨን ቼንግ ቀደም ብለው በሰጡት መረጃ መሰረት፥ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከቀኑ 4 ሰዓት ጀምሮ በዋይት ሃውስ ውስጥ ነበሩ።

13 days ago