አንድ ሮቦት በፖላንድ የዱር አሳማዎችን ከከተማ በማባረር መነጋገሪያ ሆኗል
ኤድዋርድ ዋርቾኪ የተባለ አንድ ሰው መሰል ሮቦት፣ በፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሳው በሚገኙ የመኖሪያ መንደሮች ውስጥ የዱር አሳማዎችን ሲያባርር የተቀረጸና በሮቦቱ ማሕበራዊ ትስስር ገጽ የተለቀቀ ቪዲዮ በበይነመረብ ላይ አነጋጋሪ ሆኗል።
በዋርሳው ከተማ የዱር አሳማዎች በብዛት መታየታቸው አሳሳቢ ችግር እየሆነ በመምጣቱ እንስሳቱን ያለምንም ጉዳት ወደ ጫካው መልሶ ለማባረር ይህ ያልተለመደ የሮቦት ዘዴ ስራ ላይ ውሏል።
በዋርሳው ከተማ የዱር አሳማዎች በተደጋጋሚ ምግብ ፍለጋ ወደ ከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች እና ተሽከርካሪ ማቆሚያዎች የሚገቡ ሲሆን በሰፊው በተሰራጨው ቪዲዮ ላይ ኤድዋርድ አሳማዎቹን በተጫዋችነት ስሜት ግን ደግሞ በቁርጠኝነት ሲያሳድዳቸው ይታያል።
ሮቦቱ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን የሚጠቀም ሲሆን፥ እንስሳቱ ፈርተው ወደጫካ እንዲሸሹ ለማድረግ እግሩን መሬት ላይ እየመታ “ከዚህ ሂዱ!” እያለ በፖላንድኛ ሲጮህ ተሰምቷል።
የቻይናው የቲክኖሎጂ ድርጅት ዩኒትሪ ምርት የሆነ G1 ሞዴል ሮቦት የሆነው ኤድዋርድ፥ በአሁኑ ጊዜ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ተከታይ ያለው ተጸዕኖ ፈጣሪ መሆን የቻለ ሲሆን፣ አብዛኛውን ጊዜ የስፖርት ቦርሳ አግቶ እና የአልማዝ ፈርጦች ያሉት ሮሌክስ የእጅ ሰዓት አድርጎ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀስና ከሰዎች ጋር ሲያወራ ብዙ ጊዜ ይታያል።
ኤድዋርድ የዱር እንስሳትን የመቆጣጠር ስራውን ከማከናወኑ ባሻገር፣ በፖላንድ የጠዋት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እና የዳንስ ውድድር ላይ በመቅረብ ትልቅ ዝናን አትርፏል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ- ዳንኤል መኮንን
seledadotio

13 days ago