የዓለም አጭሯ ሴት በግራፊክ ዲዛይን በከፍተኛ ውጤት ተመረቀች
በ72 ሴንቲ ሜትር ቁመት በጊነስ ወርልድ ሪከርድስ የዓለም አጭሯ በራሷ መንቀሳቀስ የማትችል ሴት ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው አሜሪካዊቷ ዊልዲን አውሞይት፥ በቨርጂኒያ ከሚገኘው ሊበርቲ ዩኒቨርሲቲ በግራፊክ ዲዛይን የመጀመሪያ ዲግሪዋን አግኝታለች።
ዊልዲን የዓለማችን አጭሯ ፕሮፌሽናል ሞዴል በመሆንም የምትታወቅ ሲሆን አሁን ደግሞ ከአራት ዓመታት የዩኒቨርሲቲ ቆይታ በኋላ፣የግል የግራፊክ ዲዛይን ሥራዋን ለመጀመር ዝግጅቷን ጨርሳ የራሷን ድረ-ገጽ በይፋ አስመርቃለች።
ዊልዲን ስለ ስኬቷ ስትናገር፥ "ትምህርቴን በማጠናቀቄ በጣም ደስ ብሎኛል። መንገዱ ረጅም ቢሆንም፣ መጨረሻው የሚያስደስት ነው" ብላለች።
ዊልዲን ከምርቃቷ በኋላ ያቀደቻቸውን ግቦች፥ ቋሚ ሥራ ማግኘት፣ የራሷን የግራፊክ ዲዛይን ድርጅት በይፋ ማስጀመር፣ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲ ስትገባ ያቋረጠችውን የሞዴሊንግ ስራ በድጋሚ በመጀመር በኒውዮርክ ፋሽን ሳምንት መድረክ ላይ መታየት እና ትልልቅ የማስታወቂያ ሥራዎችን መሥራት መሆናቸውን ገልጻለች።
ዘገባው የጊነስ ወርልድ ሪከርድስ ነው
በ- ዳንኤል መኮንን
seledadotio

14 days ago