ሰላም! እንዴት አመሻችሁ?
----------------------------
የአረንጓዴ አብዮት….
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያንን ከዳር እስከ ዳር ለተመሳሳይ ሀገራዊ ዓላማ ያሰለፈ ታላቅ ሀገራዊ አብዮት ነው፡፡
ይህ ታላቅ የተፈጥሮ ሀብት የልማት እቅድ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ትኩረት እና አድናቆት ያገኘ የአካባቢ ጥበቃ ሞዴል ለመሆን በቅቷል።
ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ የደን ሽፋንን ለማሳደግ እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ውሏል፡፡
በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረ ይህ ብሔራዊ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም፣ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች እንዲተከሉ ምክንያት ሆኗል።
በዘመቻው በተከናወኑ ተከታታይ ስራዎች የሀገሪቱ የደን ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ አድጎ 23.6 በመቶ ደርሷል።
በዚህ ዓመት የሁለተኛው ምዕራፍ ማብቂያ በአጠቃላይ 50 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የታለመ ሲሆን፣ ይህም በየዓመቱ በአማካይ 7.5 ቢሊዮን ችግኞች ይተከላሉ እንደ ማለት ነው።
ሐምሌ 2017 ዓ.ም በተደረገ የአንድ ቀን ታላቅ የችግኝ ተከላ ዘመቻ ብቻ ከ714 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በአንድ ጀምበር በመትከል አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ተመዝግቧል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ ከማልበስ ባለፈ ለኢኮኖሚ እመርታ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቷል። በመርሃ ግብሩ የተተከሉት ችግኞችም ያለምክንያት አልተተከሉም፡፡
ከ56 በመቶ በላይ የሚሆነው የጥምር ደን እርሻ ሲሆን፣ ለአርሶ አደሩ ተጨማሪ ገቢና የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጡ እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ እና ፓፓያ ያሉ የፍራፍሬ ችግኞች እንዲሁም ለመኖ የሚያገለግሉ ዕፅዋትን ያካተተ ነው።
ሌላኛውና ሁለተኛው አይነት ለአፈር ጥበቃ፣ ለውሃ አካላት መነቃቃት እና ለአካባቢ ጥበቃ የሚውሉ የሀገር በቀል የእፅዋት ዝርያዎች ናቸው።
ሦስተኛው እና በምክንያት የተተከሉት የችግኝ አይነቶች ለከተማ ውበት የሚውሉት ያጠቃልላል፡፡ እነዚህም የከተማ የአየር ንብረትን ለማስተካከል እና ለጽዳትና ውበት የተተከሉ ዛፎች ናቸው።
ችግኝ በመትከላችን የውሃ አካላትን ማዳን ችለናል፡፡ ከሀገራችን ተርፈንም የበረሃማነትን መስፋፋት ከጎረቤት ሀገራት ጋር በጋራ ለመግታት፣ ቀጣናዊ አጋርነቷን በመፍጠር አህጉራዊ ትስስርን ማሳደግ ችለናል፡፡
በዚሁ በርትተን ከቀጠልን የሀገራችን የደን ሽፋን አሁን ካለው በላይ በማሳደግ ከዓለም አቀፍ የካርበን ሽያጭ ልማት የምናገኘው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እያደገ ይመጣል።
ይህንንም ለማሳካት አሁን ያለውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከአበው ብሂል ጋር ማስተሳሰር ያሻናል፡፡
በእኛ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ችግኝ መትከልና መንከባከብ ትልቅ ስፍራ ይሰጠዋል፡፡
አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ዙሪያን ብንመለከት ከጥንት ጀምሮ በዛፍ የመሸፈን ባህል አለን፡፡
ገዳ ስርዓት ለዛፍ ትልቅ ስፍራ ይሰጣል፡፡ ያለ አግባብ ዛፍ የቆረጠ ሰው መቀጮው ከባድ ነው፡፡
በሀገራችን ዛፍ ከጥላነት ያለፈ ትርጉም አለው፡፡ በህይወት እያለን ጥላ ከለላ፣ በዘላቂ ማረፊያም በጥንት እንደ ምልክት ይተከል ነበር፡፡
ዛፍን ለሽምግልና እና ለባህላዊ ስነ-ስርዓቶች መጠቀም የተለመደ ነው። ቤተሰብ ለቀጣይ ልጆቻቸው መሬት ሲያወርሱ ዛፍ ተክለው የማስረከብ የቆየ ልማድ አላቸው።
በመሆኑም መልካም ባህላችንን ከአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ጋር በመደመር የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ህልማችንን እናሳካለን፡፡

16 days ago