ተወዳዳሪ እና ዘላቂ የቱሪዝም መዳረሻ የሆነችው ኢትዮጵያ…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ተወዳዳሪ እና ዘላቂነት ያለው የቱሪዝም መዳረሻ ናት አሉ በቱሪዝም ሚኒስቴር ስትራቴጂክ ጉዳዮች አማካሪ ቴዎድሮስ ደርበው።
አቶ ቴዎድሮስ ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት÷ በቱሪዝም ዘርፍ ተወዳዳሪነትና ዘላቂነት ወሳኝ መስፈርቶች ናቸው።
ተወዳዳሪነት ሲባል ምቹ፣ ተመራጭና ተደራሽ የቱሪዝም መስህቦች እና ለቱሪዝም የተመቸ ማህበረሰብ መኖር ሲሆን÷ ይህም የአገልግሎት ጥራት፣ ቅልጥፍናና የመስህብ ብዝኃነትን ያካትታል ብለዋል።
ቱሪዝም መዳረሻዎች ተፈጥሯዊ እና የባሕል መገለጫዎችን በመጠቀም ለቀጣዩ ትውልድ ማቆየት መቻል ለዘላቂ ቱሪዝም ወሳኝ መሆኑንም አስረድተዋል።
በተሳሳተ መንገድ የተመራ ቱሪዝም አደገኛና ባሕልን በመሸርሸር ማህበረሰባዊ ቀውስ እንዲሁም ሥነ ምህዳራዊ መራቆትን እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።
በቱሪዝም መስህቦች አካባቢ የሚኖሩ ሕዝቦች ከዘርፉ ተጠቃሚ መሆናቸው መዳረሻውን በመጠበቅ እና በመንከባከብ ረገድ ቁልፍ ሚና እንዳለው አንስተዋል።
በለውጡ መንግሥት የቱሪዝም ዘርፍ የሚታይበት መነፅር እንደተለወጠና ለኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ ሚና እንዳለው ግንዛቤ መወሰዱን ጠቅሰው÷ በዚህም ለቱሪዝም ከ5ቱ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ምሶሶዎች እኩል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በቱሪዝም ሀብት ብዝኃነት የአፍሪካ ቁንጮ የሆነችው ኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን የተጀመረው የመሰረተ ልማት ማስፋፋትና ጥራት ያለውን አገልግሎት ማቅረብ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
በቴዎድሮስ ሳህለ
አቶ ቴዎድሮስ ደርበው ከፋና ፖድካት ጋር ያደረጉትን ሙሉ ቆይታ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ይከታተሉ👇
https://www.youtube.com/wa...

20 days ago