Logo
EBC
ማሞ ለማ እና መልክናት ውዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የ8 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ውድድርን አሸነፉ
******************
የአፍሪካ ግዙፉና የሀገራችን ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተመሰረተበትን 80ኛ ዓመት አስመልክቶ ያዘጋጀው የ8 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ መነሻውን ሳር ቤት፣ መዳረሻውን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አድርጎ ተከናውኗል።

"80 ዓመታት የዘለቀ አስተማማኝ አገልግሎት፤ ዘመን ተሻጋሪ ቅርስ" በሚል መሪ ቃል በተከናወነው የሩጫ ውድድር ላይ ታዋቂ አትሌቶች፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የአየር መንገዱ ሰራተኞች፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የስፖርት ቤተሰቦች ተሳትፈዋል።

ውድድሩ "8 ኪሎ ሜትር ለ80 ዓመታት የላቀ አገልግሎት" በሚል ተምሳሌትነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ አየር መንገዱ እ.ኤ.አ ከ1946 ጀምሮ እስከ 2026 ዓ.ም የዘለቀውን የላቀ የዓለም አቀፍ የአቪየሽን ስኬት የዘከረበት ሆኗል።

በውድድሩም በታዋቂ አትሌቶች ዘርፍ በወንዶች ማሞ ለማ ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን፣ በሴቶች ደግሞ መልክናት ውዱ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሸናፊ ሆነዋል።

በዮሴፍ ሹምዬ
#ethiopianairlines #flyethiopian #athlete #athletics

20 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.