Logo
FBC
ቼልሲ አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶን ለመሾም ተስማማ

‎አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቼልሲ ስፔናዊውን አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የክለቡ አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም ከስምምነት ደርሷል፡፡

አሰልጣኙ በምዕራብ ለንደኑ ክለብ እስከ ፈረንጆቹ 2030 የሚያቆውን የአራት ዓመት ውል እንደሚፈርም ተገልጿል።

ቼልሲ በሚቀጥሉት ቀናት የአሰልጣኙን ቅጥር ይፋ እንደሚያደርግ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡

የ44 ዓመቱ አሰልጣኝ ከዚህ ቀደም ሪያል ማድሪድ እና ባየር ሊቨርኩሰንን ማሰልጠኑ ይታወሳል፡፡

ቼልሲ አሰልጣኝ ሊያም ሮሲኒየርን ካሰናበተ በኋላ አሎንሶን ጨምሮ አንዶኒ ኢራኦላ፣ ማርኮ ሲልቫ እና ኦሊቨር ግላስነር ከመሳሰሉ አሰልጣኞች ጋር ስሙ ሲነሳ ቆይቷል፡፡

ቼልሲ በዛሬው ዕለት በኤፍ ኤ የፍጻሜ ጨዋታ በማንቼስተር ሲቲ በመሸነፍ ዋንጫውን ያጣ ሲሆን የውድድር ዓመቱን ያለዋንጫ ማጠናቀቁ ተረጋግጧል፡፡

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.