የኢትዮጵያ ቀዳሚ የኢንቨስትመንት ማዕከል የመሆን ጉዞ…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ተስፋዋን ወደ ተግባርና ወደ እውነተኛ አፈጻጸም በመቀየር ቀዳሚ የኢንቨስትመንት ማዕከል የመሆን ጉዞዋን እያፋጠነች ትገኛለች።
ተግባራዊ ያደረገችው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የውጭ ባለሀብቶች በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ምህዳር ላይ ያላቸውን እምነት በከፍተኛ ደረጃ ከፍ ያደረገ ሆኗል።
በቅርቡ በአዲስ አበባ የተካሄደውና 4ኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ፎረም ለዚህ ማሳያ ተደርገው ከሚቀርቡ እውነታዎች አንዱ ነው፡፡
በፎረሙ ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በልዩ ልዩ ስትራቴጂያዊ ዘርፎች ከ13 ቢሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው የኢንቨስትመንት ስምምነቶች ተፈርመዋል።
ይህም ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎችና የቢዝነስ መሪዎች በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ምህዳር ያላቸውን ጥልቅ እምነት በተግባር ያሳየ ነው፡፡
በአምራች ዘርፍ፣ በግብርናና አግሮ ፕሮሰሲንግ፣ በታዳሽ ኃይል፣ በኮንስትራክሽን እና በማዕድን ዘርፎች ላይ የተፈረሙት እነዚህ ስምምነቶች የኢኮኖሚውን የዕድገት ጉዞ ይበልጥ የሚያፋጥኑ ናቸው፡፡
ፕሮጀክቶቹ ወደ ስራ ሲገቡ በሚሊየን ለሚቆጠሩ ወጣቶች የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር፣ የወጪ ንግድን በማሳደግ፣ ዘመናዊ አሰራርና ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት የኢንዱስትሪዎችን አቅም በማዘመን ረገድ ዘላቂ ፋይዳ ይኖራቸዋል።
በተመሳሳይ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ተመሳሳይ ፎረም ላይ የተፈረሙት የ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ስምምነቶች በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ገብተው ለሀገር ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፡፡
ይህም ከስምምነት ባሻገር የኢትዮጵያን አፈጻጸም ይበልጥ እምነት የሚጣልበት ያደርገዋል።
ይህ የኢንቨስትመንት ፍሰት ኢትዮጵያ ለቢዝነስ ዝግጁ መሆኗንና በአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለመሆን በፅናት እየተጓዘች ያለች ሀገር መሆኗን ለዓለም ያበሰረ ነው።
በሶስና አለማየሁ

21 days ago