Logo
YenetaTube
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ግንቦት 09 ቀን 2018 ዓ.ም በሸገር ከተማ የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፡-

✅ከጠዋቱ 2:30 እስከ 9:30

👉ዋልያ ብረታ ብረት ዴዲኬትድ መስመር፣ አየይካ አዲስ፣ አይካ ጀርባያሉ ኢንዱስትሪዎች፣ ዓለም ገና ፣ ኢንዱስትሪ መንደር ፣ ፉሪ ሬዲዮ ጣቢያ ፣ፉሪ፣ ሃጂ ሪልስቴት አካባቢ፣ ወርዶፋ ሎጅ፣

👉ዳርፉር ሰፈር፣ ጀሞ 2፣ ጀሞ-3 በከፊል ፣ ፋና ውሃ ስታንድባይ፣ ስላ ከብት እርባታ፣ ወለቴ ኢንዱስትሪ መንደር እና አካባቢው ላይ የሀይል አቅርቦት ይቋረጣል።

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪ መለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን።

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.