በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ባለሀብቶች ጥሬ እቃዎችን ከቀረጥ ነጻ እንዳያስገቡ መከልከላቸው ለከፍተኛ ኪሳራ እንደዳረጋቸው ተገለጸ
በትግራይ ክልል ኢንቨስት የሚያደርጉ ባለሀብቶች ለግንባታ ስራ የሚያገለግሉ እና ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ተፈቅደው ወደብ ላይ የደረሱ ጥሬ ዕቃዎችን ወደ ሐገር ውስጥ እንዳያስገቡ መከልከላቸውን የክልሉ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል።
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ዳንኤል መኮንን ለአሐዱ ሬዲዮ እንደተናገሩት፣ በክልሉ ባለው ፖለቲካዊ ውጥረት ምክንያት መንግስት የፈቀደው የኢንቨስትመንት ማበረታቻ መመሪያ በተግባር ላይ እየዋለ እንዳልሆነ ገልጸዋል።
ከተከለከሉት ጥሬ ዕቃዎች መካከልም ለኮንስትራክሽን፣ ለአሉሚኒየም ነው አልሙኒየም ስራዎች፣ ለግንባታ የሚሆን ብረት፣ ለመስታወትና ለሴራሚክ ስራዎች የሚያገለግሉ ግብዓቶች እንደሚገኙበት ጠቁመዋል።
በሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች የሚገኙ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ማበረታቻውን ተጠቅመው ጥሬ ዕቃዎችን ከቀረጥ ነፃ እያስገቡ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በትግራይ ክልል ተመሳሳይ መብት መከልከሉ ተገቢ እንዳልሆነ ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።
በዚህ ዕገዳ ምክንያት በርካታ ባለሀብቶች ያስገቧቸው ጥሬ ዕቃዎች ከወደብ እንዳይገቡ መከልከላቸው ለባለሀብቶቹም ሆነ ለሀገር ትልቅ ኪሳራ መሆኑን አቶ ዳንኤል ገልጸዋል።
ከቀረጥ ነፃ የመግባት መብቱ መገደቡ የክልሉን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እያቀዛቀዘው መሆኑን በመጥቀስ፣ ችግሩ እንዲፈታ ለገንዘብ ሚኒስቴር ጥያቄ ቢቀርብም እስካሁን ምንም ዓይነት ምላሽ አለመገኘቱን አስታውቀዋል።
#አሐዱ

22 days ago