(ዘ-ሐበሻ ዜና) የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (ዩኤኢ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በኢራን ጦርነት ወቅት አገሪቱን በሚስጥር ጎብኝተዋል በማለት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት የወጣውን መግለጫ "ፈጽሞ መሰረት የሌለው" ሲል አጥብቆ አስተባብሏል።
ሚኒስቴሩ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ "ዩኤኢ ከእስራኤል ጋር ያላት ግንኙነት ግልጽ እና በይፋ በታወጀው 'የአብርሃም ስምምነት' ማዕቀፍ ውስጥ የሚመራ እንጂ፣ ግልጽነት በጎደላቸው ወይም መደበኛ ባልሆኑ ስምምነቶች ላይ የተመሰረተ አለመሆኑን በድጋሚ ታረጋግጣለች" ብሏል።
አክሎም "በመሆኑም በሚመለከታቸው የዩኤኢ ባለስልጣናት በይፋ ካልተገለጸ በስተቀር፣ ስለተደረጉ ሚስጥራዊ ጉብኝቶች ወይም ይፋ ስላልተደረጉ ስምምነቶች የሚነሱ ማናቸውም መረጃዎች ሙሉ በሙሉ መሰረት የሌላቸው ናቸው" ሲል አብራርቷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በመግለጫው ማጠቃለያ ላይ፣ መገናኛ ብዙሃን (ሚዲያዎች) ትክክለኛነትን እና ሙያዊ ስነ-ምግባርን እንዲላበሱ፣ እንዲሁም ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ከማሰራጨት ወይም አሳሳች የፖለቲካ ትርክቶችን ከማራመድ እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቧል።

23 days ago