የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ብቻ ሊከናወን ነው
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች የዲግሪ ሰርተፊኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ብቻ ሊከናወን መሆኑ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር)እንዳሉት፤ አሰራሩ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃን ለመከላከል ያለመ ነው፡፡
ከዚህ በፊት ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጨረታ ባሸነፈ ድርጅት በኩል የተማሪዎችን የትምህርት ማስረጃ የሚያሳትሙበት አሰራር ለሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አጋላጭ ሆኖ ቆይቷል ብለዋል፡፡
በመሆኑም ሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎቻቸውን ዲግሪ በአንድ ማዕከል ብቻ እንዲያሳትሙ ይደረጋል ብለዋል፡፡
አዲሱ ዲግሪ ታትሞ እስኪደርስ ድረስ ትምህርት ሚኒስቴር ዲግሪ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የድጋፍ ደብዳቤ እንደሚጽፍ ገልጸው፤ ህትመቱ በዚህ ዓመት እንደሚጀምር ጠቁመዋል።
በ2017 ዓ.ም የተመረቁ ተማሪዎችን ጨምሮ ከዚህ በኋላ የሚመረቁትም ሙሉ በሙሉ በአዲሱ ስርዓት መሰረት በአንድ ማዕከል የሚታተመውን ዲግሪ ብቻ እንዲወስዱ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ ከ2017 ዓ.ም በፊት ተመርቀው ነገር ግን ዲግሪያቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎች በአዲሱ አሰራር ብቻ እንደሚስተናገዱ አመልክተዋል።
ፋና
seledadotio

25 days ago