የዋንጫው ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ፡ አርሰናል በለንደን ደርቢ ከዌስትሃም ዩናይትድ
**************
ሊጠናቀቅ የሁለት ጨዋታዎች ዕድሜ ብቻ በቀረው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ፣ ለሻምፒዮንነት የሚደረገው ትግል አሁንም በአጓጊነቱ ቀጥሏል። "አርሰናል ወይስ ማንችስተር ሲቲ?" የሚለው ጥያቄ ምላሽ ለማግኘት ጥቂት ሳምንታት የቀሩት ሲሆን፤ ሊጉን በ76 ነጥብ እየመራ የሚገኘው አርሰናል፣ ዛሬ ምናልባትም የዋንጫ ጉዞውን ትክክለኛ መዳረሻ ፍንጭ ሊሰጥ የሚችለውን ወሳኝ ጨዋታ በለንደን ደርቢ ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ያደርጋል።
አርሰናል ከ22 ዓመታት በኋላ ሻምፒዮን ለመሆን፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ደግሞ በሊጉ ለመቆየት የሚፋለሙበት መሆኑ መርሃ ግብሩን እንዲጠበቅ ያደርገዋል። መድፈኞቹ በፕሪሚየር ሊጉ ከኤቨርተን በመቀጠል ብዙ ጊዜ ያሸነፉት ዌስትሃምን ሲሆን፤ በለንደን ስታዲየም ባደረጓቸው ያለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎችም 11 ግቦችን አስቆጥረው አሸንፈዋል። በተጨማሪም መድፈኞቹ ከዌስትሃም ከሜዳቸው ውጭ ባደረጓቸው ያለፉት 17 ጨዋታዎች የተሸነፉት አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
ዌስትሃም ምንም እንኳን በወራጅ ቀጠናው ውስጥ ቢገኝም፣ በሜዳው ባደረጋቸው ያለፉት ስድስት ጨዋታዎች አለመሸነፉ ዛሬ ለአርሰናል ከባድ ፈተና ሊሆን ይችላል። ለሁለቱም ቡድኖች የህልውና ያህል ወሳኝ የሆነው ይህ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ከ30 ላይ የሚጀመር ሲሆን፤ ለምሽቱ ፍልሚያ ካይ ሃቨርትዝ እና ማርቲን ኦዴጋርድ ዝግጁ መሆናቸውን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አረጋግጧል። ዩሪየን ቲምበር ግን አሁንም ከጉዳቱ አልተመለሰም።
አርቴታ ከጨዋታው በፊት በሰጠው አስተያየት "ለዋንጫው እጅግ የቀረብንበት ሰዓት በመሆኑ፣ በውድድር ዘመኑ ሁሉ ካሳየነው በላይ የሆነ የውጤት ረሃብና ፍላጎት አሳይተን እንጫወታለን፤ ለዚህም በሚገባ ተዘጋጅተናል" ብሏል። የዌስትሃሙ አለቃ ኑኖ እስፒሪቶ ሳንቶ በበኩላቸው "የጨዋታውን አስፈላጊነት ጠንቅቀን እንረዳለን፤ በሜዳችን የምናደርገው በመሆኑ የምንፈልገውን ውጤት የምናሳካበት ጨዋታ ይሆናል" ብለዋል፡፡
በርንሌይ ከአስቶን ቪላ፣ ክሪስታል ፓላስ ከ ኤቨርተን እና ኖቲንግሀም ፎረስት ከ ኒውካስትል ዩናይትድ ሌሎች ዛሬ በተመሳሳይ 10 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
በአንተነህ ሲሳይ

3 months ago