Logo
YenetaTube
በፖሊስ የምትፈለገው በረከት ወርቁ በሰጠችው ምላሽ በባለስልጣናት ላይ ክስ ሰነዘረች

በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በከባድ የሙስና ወንጀል ከሚፈለጉ አራት ግለሰቦች መካከል አንዷ የሆነችው በረከት ወርቁ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጿ ባስተላለፈችው መልዕክት የቀረበባትን ክስ አስተባበለች።

በረከት ወርቁ በሰጠችው ምላሽ "ምንም በማላውቀው ጉዳይ በወንጀል ተፈላጊ ሆንኩ" ስትል የገለጸች ሲሆን ፖሊስ ስምንት ሚሊዮን ብር ሀገር አሳጥተሻል በሚል ያቀረበው ክስ መሠረተ ቢስ መሆኑን ተከራክራለች።

ይልቁንም እናንተ የወሰዳችሁብኝ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ነው ስትል በባለስልጣናት ላይ የመልስ ክስ ሰንዝራለች።

በተጨማሪም አብሯት በዝርዝሩ ውስጥ ስለተጠቀሰው አቶ አቡሽ አየለ ስትገልጽ ግለሰቡ ለብሔራዊ ባንክ በኩንታል ወርቅ የሚያስገቡና 28 የወርቅ ማውጫ ያላቸው ትልቅ ነጋዴ መሆናቸውን ጠቅሳለች።

በወርቅና ነዳጅ ላይ የሚሳተፉ ጥቂት ቡድኖች ሌሎቻችን እንድንወገድ ፈርደውብናል ስትል የጉዳዩ መነሻ የጥቅም ግጭት እንደሆነ አመልክታለች።

በረከት ወርቁ በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ በወርቅ ማዕድን ልማት ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችል የኢንቨስትመንት ሰርተፊኬት እንዳላት ባያያዘችው ሰነድ ገልፃለች

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.