Logo
Zehabesha
የቀድሞው የማንቸስተር ዩናይትድ አማካይ ኦዌን ሃርግሪቭስ በቲኤንቲ ስፖርት ላይ ቀርቦ አርሰናል በቀጣይ ከፓሪስ ሴንት ዠርመን ጋር ስለሚኖረው ጨዋታ እና የማሸነፍ እድል ተከታዩን አስተያየት ሰጥቷል፡

"አርሰናል ያለምንም ጥርጥር የማሸነፍ እድል አለው። ባላቸው የተከላካይ ክፍል እና ግብ ጠባቂ እጅግ ድንቅ ናቸው። ዴክላን ራይስ በተከላካይ አማካይ ስፍራ ላይ እየተጫወተ ሲሆን፣ እዚያ ቦታ ላይ ደግሞ አስደናቂ ብቃቱን እያሳየ ነው። ጨዋታው እጅግ አጓጊ ይሆናል። ፒኤስጂ ከባየርን ሙኒክ ጋር ከነበረው ጨዋታ ይበልጥ አጥቅቶ እንደሚጫወት ይጠበቃል፤ ነገር ግን አሁን የምናየው አርሰናል የተለየ ነው። ባለፉት ሶስት ወይም አራት ሳምንታት ውስጥ ከገጠማቸው አነስተኛ መዋዠቅ (ማሽቆልቆል) አሁን ላይ ያገገሙ ይመስለኛል። አሁን በራሳቸው ያምናሉ። ቡካዮ ሳካ በትልልቅ እና ወሳኝ ሰዓቶች ላይ ትልልቅ ግቦችን ይዞ ተመልሷል። እድሉ አላቸው፤ ማድረግ ያለባቸው በራሳቸው ማመን ብቻ ነው።"

ባየርን ሙኒክ 1 - 1 ፓሪስ ሴንት ዠርመን (በድምር ውጤት 5-6)

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.