Logo
SeledaPost
ስለ ፕሮስቴት ካንሰር ግንዛቤ ለማሳደግ የመራቢያ አካሉን በመጠቀም የፖሊስ መኪና የጎተተዉ ግለሰብ መነጋገሪያ ሆኗል

ጠንካራዉ ሰው በአለም ላይ በብልቱ መኪና ለመጎተት የመጀመሪያው ሰው ሆኗል የተባለ ሲሆን ዓላማዉን ስለ ፕሮስቴት ካንሰር ግንዛቤን ለማሳደግ የተደረገ እንደሆነ ተናግሯል።

የ50 አመቱ ጆን ስቴፈን ወንድነቱን ተጠቅሞ ባለ 2 ቶን የፈረንሳይ ፖሊስ መኪና 131 ጫማ ያህል በመኖሪያ ጎዳና ላይ ጎትቷል። ይህዉ ተግባር በምዕራብ ዮርክሻየር፣ እንግሊዝ ውስጥ የተከናወነ ሲሆን ግራ የተጋቡ ነዋሪዎች ሲመለከቱ የነበረውን አስገራሚ ፈተና አጠናቋል።

የማርሻል አርት ኤክስፐርቱ የወንዶች የጤና ጉዳዮችን ግንዛቤ ለማሳደግ በሚል አነጋጋሪ አጀንዳን ለማጣመር መወሰኑን ገልጿል፡፡"አልዋሽም፤ ትንሽ ጎድቶኛል" ነገር ግን አእምሮዬ አተኩሮ ነበር እናም ወደ 40 ሜትሮች ተሸከርካሪዉን ጎትቼዋለሁኝ ማለቱን ዳጉ ጆርናል ዘግባል።

የፕሮስቴት ካንሰር በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በወንዶች ላይ በጣም የተለመደ ካንሰር ነው፡፡ ለወንዶች በካንሰር ረገድ ሁለተኛዉ የሞት ምክንያት ነው። ከ 6 ወንዶች መካከል አንዱ በህይወት ዘመኑ የፕሮስቴት ካንሰር ምርመራ እና ህክምና ሂደት ዉስጥ ያልፋል፡፡

በኤደን ሽመልስ

seledadotio
seledadotio
3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.