(ዘ-ሐበሻ ዜና) ‹‹በማንኛውም አገር ላይ ፀብ ማንሳት አንፈልግም፣ ነገር ግን ማንም ይሁን በእኛ ላይ ጥቃት የፈፀመ ምላሹን ያገኛል›› ሲሉ የሱዳን ባለስልጣናት ተናገሩ፡፡ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትርና የጦር ሀይሉ ቃል አቀባይ ትላንት ምሽት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን በዚህ መግለጫ ላይ የተነሱትን ሀሳቦች ሬዲዮ ዳባንጋ በአጭሩ አቅርቧቸዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሞሂ አልዲን ሰላም በመግለጫቸው በካርቱም አየር ማረፊያ ላይ ትላንት ለተፈፀመው ጥቃት ኢትዮጵያና ዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ ተሳታፊ መሆናቸውን መግለፃቸውን የጠቀሰው ዘገባው ‹‹በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኤመሬትስ ላይ ለከፈትነው ክስ ይህንን ማስረጃ አድርገን እናቀርባለን›› ማለታቸውን አስረድቷል፡፡
ጨምረውም ‹‹የትላንቱ ድርጊት እኛ እንደእህት ከምናያት ኢትዮጵያ ወረራ እንደተካሄደብን ማረጋገጫ ነው›› ያሉት ሚኒስትሩ ይህን ጥቃት የተፈፀመው ‹‹ጠላቶች›› ያሏቸው አካላት ሰዎች ወደካርቱም በፈቃደኝነት እየተመለሱ መሆኑን በማየት የፈፀሙት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በማስከተልም ‹‹ኢትዮጵያና ኤመሬትስ የተሳሳተ መንገድን መርጠዋል፡፡ በዚህ ደግሞ ይቆጫቸዋል›› ያሉት ሚኒስትሩ በተለይ የኢትዮጵያ መንግስት የሁለቱን አገራት ግንኙነት እንዳበላሸ አድርገው መግለፃቸውን ዘገባው አስታውቋል፡፡
ጨምሮም ለዚህ ድርጊት ተመጣጣኝ መልስ የመስጠት ህጋዊ መብት እንዳላቸው ያስረዱት ሚኒስትሩ ‹‹በማንኛውም አገር ላይ ፀብ ማንሳት አንፈልግም፣ ነገር ግን ማንም ይሁን በእኛ ላይ ጥቃት የፈፀመ ምላሹን ያገኛል›› ማለታቸውን ጠቅሷል፡፡ የሱዳን ጦር ሀይል ቃል አቀባይ የሆኑት ብርጋዴር ጄኔራል አሲም አውድ አብደልዋሀብ በበኩላቸው በንባብ ባሰሙት መግለጫ ከተለያዩ መረጃዎችና ሪፖርቶች በመነሳት ድርጊቱ የተጀመረው በማርች ወር መጀመሪያ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ጨምረውም 3 ድሮኖች ከባህር ዳር ተነስተው በኋይት ናይል፣ ብሉ ናይል፣ ሰሜንና ደቡብ ኮርዶፋን ግዛቶች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን አውስተዋል፡፡
ከዚያም ማርች 17 ቀን ከእነዚህ ድሮኖች አንደኛው ተመቶ መውደቁንና በዚህ ድሮን ላይ በተደረገው ምርመራ አምራቹን ለመረዳት መቻላቸውን አስታውቀዋል፡፡ ይህ የመለያ ቁጥሩ ‹‹ኤስ 88›› የሆነው ድሮን ባለቤትነቱ የዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ መሆኑን ለማወቅ መቻላቸውን ጠቅሰው ድሮኑ በኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በባህር ዳር አየር ማረፊያ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን መረዳታቸውን ገልፀዋል፡፡
ካገኙት መረጃ በመነሳት ይህ ድሮን በተደጋጋሚ የሱዳንን አየር ክልል ጥሶ በኩምሩክ አካባቢና በሰሜናዊ ኮርዶፋን ጥቃት እንደፈፀመ አስረድተዋል፡፡ ቃል አቀባዩ ሲቀጥሉም ከሜይ 1 እስከ ሜይ 4 ባሉት ቀናት ደግሞ እንደገና ከባህር ዳር ተነስቶ የሱዳንን አየር ክልል በመጣስ በጀበል አውሊያ የተሰኘው አካባቢ እስከሚደርስ ድረስ ክትትል ሲያደርጉበት እንደነበር አስታውቀዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹ይህ ማስረጃ የሚያሳየው ኤመሬትስና ኢትዮጵያ የአየር ክልላችንን እንደጣሱ ነው፡፡ እንዲህ አይነት ድርጊትን በዝምታ አናልፈውም›› ሲሉም ተናግረዋል፡፡ የሱዳን ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ካሊድ አልአሲር ደግሞ የካርቱም አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሰላማዊ መሰረተ ልማት መሆኑን ገልፀው ከደህንነት ጋር የተገናኙ ቴክኒካል ጉዳዮች ካለቁ በኋላ አየር ማረፊያው መልሶ ስራ እንደሚጀምር አስረድተዋል፡፡ በአየር ማረፊያው ላይ ጉዳት ያልደረሰ ቢሆንም በብሎክ 5 በኩል ባለው መውጫ አንድ ቤት ተመቶ ሁለት ወንድማማቾች መቁሰላቸውንም አስታውቀዋል፡፡

1 month ago