አርበኝነት ለሀገር ያለ ዋጋ የሚከፈል ከራስ ወዳድነት የነጻ መሥዋዕትነት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አርበኝነት ማለት ለሀገር ያለ ዋጋ የሚከፈል ከራስ ወዳድነት የነጻ መሥዋዕትነት ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለ85ኛው የአርበኞች በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንዳሉት÷ ሚያዚያ 27 ቀን ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አርበኞች የፋሽስትን ወረራ የቀለበሱበትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ያስከበሩበት በዓል ነው።
አርበኝነት ማለት ለሀገር ያለ ዋጋ የሚከፈል ከራስ ወዳድነት የነጻ መሥዋዕትነት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ዓላማውም ሀገርንና ሕዝብን ብቻ ማዕከል ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
እናትና አባት አርበኞች ከፋሺስት ጋር የተዋጉት ለሀገር እና ለወገን ብለው ነው፤ በግል ጥቅም ለማግኘትማ ከአርበኝነት ይልቅ ባንዳነት አቋራጭ ነበር፤ ግን አላደረጉትም ሲሉም አብራርተዋል።
የአርበኝነት ትግሉ ከሦስት ጠላቶች ጋር የተደረገ ነበር በማለት ገልጸው÷ ከራስ ፍላጎት፣ ከባንዳና ከወራሪ ፋሺስት ጋር መሆኑን አስረድተዋል።
አርበኝነት የራስን ጥቅም ለሀገር ጥቅም ሲባል መተው ነው፤ የግል ክብርን፣ የግል ሥልጣንን እና የግል ጥቅምን መሠዋት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ይሄንን ለመቀበል ከጠላት በፊት ራስን ማሸነፍ ይጠይቃል ብለዋል።
ባንዳዎች ራሳቸውን ማሸነፍ ያቃታቸው ናቸው፤ የግል ጥቅምንና ክብርን ማሸነፍ ሲያቅታቸው የሀገራቸውን ክብርና ጥቅም ይሸጣሉ ሲሉም አመልክተዋል።
ባንዳነት ማለት ሀገርን ለራስ ጥቅም በመሸጥ የሚከናነቡት የውርደት ካባ ነው፤ አርበኞች ከባንዳዎች ጋር ታግለዋል፤ ባንዳዎች በአንድ በኩል ሀገራችሁን ሽጣችሁ እንደኛ በግል ተጠቀሙ ይሏቸዋል፤ በሌላ በኩል መንገድ እየመሩ ወራሪውን ያመጡባቸዋል። ያም አልሆን ሲላቸው ሕዝቡን በሐሰተኛ ወሬ ልቡን ይሰልቡባቸዋል ነው ያሉት።
ዛሬም ሦስቱም ጠላቶች አሉ፤ መልክና ስም ብቻ ቀይረዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ በሌላም በኩል ዛሬም በየመስኩ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን አርበኞች አሉ ብለዋል።

1 month ago