Logo
SeledaPost
በኮስቲ ከተማ በሚገኝ የነዳጅ ማከማቻ ላይ የድሮን ጥቃት ተሰነዘረ

​በሱዳን ዋይት ናይል ግዛት በምትገኘው ኮስቲ ከተማ፣ ራባክን በሚያዋስነው አቅጣጫ በሚገኝ የነዳጅ ማከማቻ ዴፖ ላይ የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች  የድሮን ጥቃት መፈጸማቸው ተዘገበ።

በኬናና ኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ውስጥ የሚገኙ የነዳጅ ታንከሮች እና የኤታኖል ማምረቻ ክፍሎች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፣ በቦታው ላይ ከፍተኛ የእሳት አደጋ መከሰቱ ተገልጿል።

​የሱዳን መገናኛ ብዙኃን እና ወታደራዊ ምንጮች ድሮኖቹ የተነሱት #ከኢትዮጵያ ግዛት (በተለይም ከባሕር ዳር አየር ማረፊያ) እንደሆነ በድጋሚ ክስ አቅርበዋል።የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ግንቦት 2026 በሰጠው መግለጫ፤ "ክሱ መሰረተ ቢስ ነው" በማለት ውድቅ አድርጎታል። ይልቁንም የሱዳን ጦር ለህወሓት (TPLF) ታጣቂዎች ድጋፍ እየሰጠ ነው ሲል መልሶ ከሷል።

ይህንን ክስተት ተከትሎ ሱዳን በኢትዮጵያ የሚገኘውን አምባሳደሯን ለምክክር ወደ ካርቱም መጥራቷ ተሰምቷል። ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ከፋ ደረጃ እየተሸጋገረ መሆኑን ያሳያል።

seledadotio
seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.