አብዛኛው የኤሌክትሪክ መቋረጥ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሰራር ጋር የተገናኘ እንዳልሆነ ተቋሙ ገለጸ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሀገሪቱ በአብዛኛው የሚስተዋለው የኃይል መቆራረጥ ከተቋሙ ጋር የተገናኘ እንዳልሆነ አስታውቋል።
የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በኢትዮጵያ ለሚታየው የኃይል መቆራረጥ የተለያዩ ምክንያቶች እንደሚጠቀሱ ገልጸዋል። በማስተላለፊያ መስመሮች ወይም በማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ ጥገና ሲደረግ እንዲሁም በስርቆት ምክንያት ጉዳት ደርሶ እስከሚጠገን ድረስ የኃይል መቆራረጥ ሊያጋጥም እንደሚችል ገልጸዋል።
ተቋሙ ይህንን አስቀድሞ ለህብረተሰቡ የሚያሳውቅ መሆኑን ጠቁመው ሆኖም አብዛኛው የኃይል መቋረጥ ምክንያት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተቋም ጋር የሚገናኝ አለመሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2018 ዓ.ም በ9 ወራት ውስጥ ከ27 ሺህ ጊጋ ዋት በላይ ኃይል ያመነጨ ሲሆን ከመነጨው ኃይል ውስጥ 24 ሺህ 970 ጊጋ ዋት ኃይል መሸጡን አስታውቋል።
እንደ ተቋሙ መረጃ በሀገሪቱ ለሚስተዋለው የኃይል መቆራረጥ አንዱ ምክንያት የመሰረተ ልማት ስርቆት ነው። በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ አንቀጽ 666 መሰረት የኃይል መሰረተ ልማትን መስረቅ በህግ የሚያስጠይቅ ከባድ ወንጀል ነው።
በዚህም ማንኛውም ሰው ተገቢ ያልሆነ ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የሌላ ሰው ከሆነ የኃይል ማሰራጫ ወይም ለሌላ ሰው ከተዘረጋ መስመር ላይ ጋዝ፣ እንፋሎት፣ ኤሌክትሪክ ወይም ሌላ ዓይነት ኃይል በመውሰድ የራሱ ያደረገ ወይም የተገለገለበት እንደሆነ እንደጥፋቱ አይነት በቀላል እስራት ወይም ከ5 ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት እንደሚቀጣ ተደንግጓል።
#አሐዱ

1 month ago