ማንቼስተር ሲቲ ነጥብ ጣለ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ኤቨርተን እና ማንቼስተር ሲቲ 3 ለ 3 አቻ ተለያይተዋል።
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ የኤቨርተንን ግቦች ባሪ (2) እና ኦብሬን አስቆጥረዋል።
የማንቼስተር ሲቲን ግቦች ደግሞ ጄርሚ ዶኩ (2) እና ኧርሊንግ ሃላንድ ከመረብ አሳርፈዋል።
አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ያለው ማንቼስተር ሲቲ ከሊጉ መሪ አርሰናል በ5 ነጥቦች ርቆ ይገኛል።
ማንቼስተር ሲቲ በጨዋታው ከአርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ለማጥበብ የነበረውን እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

3 months ago