Logo
FBC
ሪዞርቱ መንግሥት እና ባለሀብት የተባበሩበት፣ ሀሳብ እና ተግባር የተገናኙበት ነው- ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

ፈለገ ግዮን ኦኮ ሪዞርት ዛሬ ተመርቆ ሥራ ጀምሯል።

በምርቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል በታሪክ፣ ተፈጥሮና ባህል የታደለ መሆኑን ገልጸዋል።

መንግሥት ለቱሪዝም ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት ከጥንትም ከነበሩት ታሪካዊ ሥፍራዎች፣ ባሕላዊ እና ሃይማኖታዊ ክዋኔዎች፣ ተፈጥሯዊ መዳረሻዎች እና ጸጋዎች ባሸገር ለክልሉ ተጨማሪ ውበት እና በረከት የሚሆኑ የቱሪዝም መዳረሻዎች እየተገነቡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በአማራ ክልል የጎርጎራ እና የሎጎ ሐይቅ የተደበቀ ጸጋ መገለጡንም ገልጸዋል።

ዛሬ ደግሞ ለባሕር ዳር ከተማ እና በአጠቃላይ ለክልሉ ተጨማሪ ጸጋን የሚደርብ ሪዞርት መመረቁን ነው የተናገሩት።

የፈለገ ግዮን ሪዞርት የጣና ሐይቅን ደኅንነት፣ ውበት እና ጸጋን የጠበቀ፣ ተጨማሪ ውበት የሆነ የጥራት ደረጃው በባለሙያዎች የተመሰከረለት መኾኑን ገልጸዋል።

የፈለገ ግዮን ሪዞርት እና ሌሎች የልማት ሥራዎች እንዲሠሩ ላደረጉ ሁሉ ምሥጋና አቅርበዋል።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.