መከላከል እና አክሞ ማዳን የጤና ፖሊሲን በመቅረጽ ተግባራዊ አድርገናል - ዶ/ር መቅደስ ዳባ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዓመታት በሽታን መከላከል እና አክሞ ማዳን የጤና ፖሊሲ ተቀርጾ ተግባራዊ ተደርጓል አሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፡፡
ሚኒስትሯ “የማህበራዊ ልማት እመርታ ለሀገር ግንባታ’’ በሚል መሪ ሐሳብ በተዘጋጀውና በማህበራዊ ዘርፍ ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ዐበይት ውጤቶች በሚቀርቡበት የምክክር መድረክ ላይ ባቀረቡት ማብራሪያ ነው ይህንን የገለጹት።
ከለውጡ መንግሥት በፊት የነበረው የጤና ፖሊሲ በሽታን መከላከል ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር መቅደስ÷ በለውጡ መንግሥት በጤናው ዘርፍ በርካታ ሪፎርሞች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በዚሁም በሽታን መከላከል እና አክሞ ማዳን የጤና ፖሊሲ ትግበራ ዋነኛው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት የጤና መሰረተ ልማቶች ግንባታ በብዛት እና በጥራት መገንባታቸውን አንስተው÷ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር መደረጉንም አመላክተዋል፡፡
ከለውጡ በፊት 7 ሺህ ብቻ የነበሩት የግል ጤና ተቋማት በአሁኑ ሰዓት ከ30 ሺህ በላይ መድረሳቸውን አስረድተዋል፡፡
በለውጡ ዓመታት በአጠቃላይ ከ13 ሺህ በላይ የጤና መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች መገንባታቸውን ገልጸው÷ የጽኑ እና ድንገተኛ ህክምና ማዕከላት፣ ዘመናዊ ላቦራቶሪዎች፣ የጽዱ ጤና ተቋማት እና መሰል ግንባታዎች ተከናውነዋል ብለዋል።
ለሕብረተሰቡ የሚቀርቡ 44 በመቶ መድኃኒቶች በራስ አቅም በሀገር ውስጥ ተቋማት የሚመረቱ መሆናቸውን በመግለጽ ይህም ሀገሪቱ የጤና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት አጋዥ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
የወረርሽኝ ልየታ እና ቁጥጥርን ጨምሮ ባለፉት ዓመታት በዘርፉ የተሰሩ ስራዎች አመርቂ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በአቤል ነዋይ

1 month ago